Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ሚኒስቴር በፌዴራል ሆስፒታሎች የስራ አፈጻጸምና የጤና ባለሙያዎችን ማበረታቻ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ

CERPHI

የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር እና የጤና ባለሙያዎችን ደህንነትን ለማሻሻል የታለሙ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ከፌዴራል ሆስፒታሎች አመራሮች ጋር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደ/ር ደረጀ ዱጉማ በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱ በዋናነት ያተኮረባቸው ጉዳዮች የሆስፒታሎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ (Duty Payment) መመሪያ አፈጻጸም ሁኔታ፣ የግል ህክምና (Private Wing Service) አገልግሎት ማስፋፋት፣ የሰራተኞች መኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የካፊቴሪያ እና የተረኛ ባለሙያዎች ማረፊያ ማሻሻያዎች፣ የሆስፒታል እድሳት እና የነዳጅ አስተዳደርን ያካተቱ ከደመወዝ ውጪ የሆኑ የማበረታቻ ፓኬጆች ትግበራ ላይ ነው።

በበርካታ የፌዴራል ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎችን የስራ አካባቢ እና ተነሳሽነት ለማሻሻል የሚያስችሉ አበረታች አፈጻጸሞች የታዩ ሲሆን፤ በአንፃሩ አፋጣኝ እርምጃ የሚሹ ክፍተቶችም በውይይቱ ተለይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረጉ የድጋፍና ክትትል ግኝቶች ቀርበው ጠቃሚ ተሞክሮዎችና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ታይተዋል።

የሆስፒታል አመራሮች በተለይም የትርፍ ሰዓት ክፍያ መመሪያ ትግበራ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ተግባራዊ ተግዳሮቶችን ያነሱ ሲሆን፤ በምላሹም ክቡር ዶ/ር ደረጄ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮችን በዝርዝር አይተው መፍትሄ እንዲያቀርብ ለቴክኒክ ቡድኑ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የግል ህክምና (Private Wing Service) አገልግሎት ማማሪያ ተሻሽሎ በቅርብ ጊዜ በሁሉም ፌዴራል ተቋማት አንደሚተገበር የተገለጸ ሲሆን የተጀመሩ የተላያዩ ላጤና በላሙያ የሚሆኑ የማትግያ ስራዎች (ላምሳሌ የሰራተኞች መኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የካፊቴሪያ እና የማሰሳሉት) በዘላቂነት እንዲሳሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የቅርብ ክትትል እና አስፋላጊዉን ድጋፍ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በማጠቃለያም ተነሳሽነት እና ብቃት ያለው የጤናው ዘርፍ ባለሙያን ማዕከል ያደረገ፣ ጠንካራ እና ፈጣን ምላሽ ሰጪ የጤና ስርአት ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እነዚህ የሪፎርም ስራዎች የባለሙያውን እርካታ እና አጠቃላይ የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ቁልፍ በመሆናቸው ሁሉም ተቋማት ጥብቅ፣ ወጥ የሆነና በተፋጠነ አፈጻጸም እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *