Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የEOC ስብሰባውን አካሄደ

CERPHI

ኢንስቲትዩቱ ሳምንታዊ የአደጋ ምላሽ ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ስብሰባውን በማካሄድ፣ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ የሕብረተሰብ ጤና ሁኔታ፣ የበሽታ ክትትልና ቅኝት፣ የወረርሽኝ ሁኔታ እንዲሁም እየተከናወኑ ያሉ የምላሽ እርምጃዎችን ገምግሟል።

የኢንስቲትዩቱ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የዚህን ሳምንት ቅኝት ሲያብራሩ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የወባ ስርጭት ለመቆጣጠር ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

የአጎበር አጠቃቀምን ማጠናከር፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማፋሰስ እና ማዳፈን ፣ የተለያዩ የአካባቢ ጽዳትና የመከላከል ሥራዎችን ማጠናከር ፣ እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ አካባቢዎች የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የወባ ተጠርጣሪ ታካሚዎችን በትክክል ለይቶ ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት፣ በጤና ተቋማት የሚሰጡ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም አቶ ወልደሰንበት አንስተዋል።

በተጨማሪም ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች ተገቢውን ክትትልና ሕክምና በመስጠት ፈጥነዉ ማገገም እንዲችሉ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል፣ በክልሉ የሚከሰቱ የውሻ ንክሻ ክስተቶችን በቅርበት በመከታተል የቅድመ መከላከልና የፈጣን ምላሽ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሥርዓተ ምግብ ጫና ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት፣ ሕፃናት ለምግብ እጥረት እንዳይጋለጡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ተነስቷል።

በስብሰባው ባለፈው ሳምንት የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተገምግመዋል።

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *