Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

CERPHI

በኢንስቲትዩቱ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ መሪነት በተካሄደው በዚህ የግምገማ መድረክ፤ በሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ፣ በሕብረተሰብ ጤና ምርምር፣ በላቦራቶሪ አገልግሎት እንዲሁም በጤና መረጃ አስተዳደር ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሮቹ የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ከወዲሁ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመው፣ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በተቋሙ የስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ ኃላፊ በወ/ሮ ሂወት አበበ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የማኔጅመንት አባላቱ በጥልቀት ተወያይተውበታል። በዚህም መሠረት ከ2018 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፡የወባ ታማሚዎች ቁጥር በ47.3% ፣የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር በ98.9%፣የማጅራት ገትር ታማሚዎች ቁጥር በ36.5% መቀነሱ በሪፖርቱ ለአብነት ተመላክቷል ።

በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፡

ሦስት ላቦራቶሪዎች የISO 15189 የዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝተዋል።

የነፃ ስልክ ጥሪ ማዕከሉ ለ11,305 ደዋዮች አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 8,115 ደዋዮች የቀጥታ የጤና ትምህርት አግኝተዋል።

12 ጥናታዊ ጽሑፎች በታዋቂ ሳይንሳዊ ጆርናሎች የታተሙ ሲሆን፣ የብሔራዊ የሊድ መመረዝ ሮድማፕ ዶክመንት ዝግጅት ተጠናቋል።

በተጨማሪም በኤች አይ ቪ የመያዝ የግለሰብ ደረጃ የቅኝት ጥናት ተካሂዷል።

በውይይቱ ማጠቃለያም የተመዘገቡ በጎ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና የተቋሙን አጠቃላይ የሪፎርም እንቅስቃሴዎች ማፋጠን እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *