Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: September 2026

CERPHI

የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሮች የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና የኢንስቲትዩትን የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC)፣ የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (VHF) ላቦራቶሪ፣ የጂኖሚክስ ላቦራቶሪ እና የስነ ምግብ ላቦራቶሪዎችን የቴክኒክ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በእውነተኛ ጊዜ ለማስተባበር፣ ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን በሽታ አምጪ ተህዋስያን ለመመርመር፣ የጂኖም ክትትልና ትንተና ለማካሄድ እንዲሁም በስነ ምግብ ዘርፍ የላብራቶሪ ምርመራና ሳይንሳዊ ድጋፍ ለመስጠት ያለውን አቅም ለተሳታፊዎቹ እንዲያውቁ አስችሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የፖሊዮ ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ አቅምን ገመገመ

WHO Delegation Reviews Ethiopia’s Polio Surveillance and Response Efforts የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተገኝቶ ጉብኝቱን ሲያካሂድ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የፖሊዮ በሽታ ክትትል (ቅኝት) እና ምላሽ አሰጣጥ እንቅስቃሴዎችን፣ የላቦራቶሪ የምርመራ አቅምን ለመመልከት እና ኢትዮጵያ ከፖሊዮ ነፃ የሆነችበትን ሁኔታና ደረጃ አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሉ የጋራ ትብብሮችን ለመገምገም እና ለማጠናከር በማለም ነው። በልኡካን ቡድኑ…
Read more

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማና በድግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 202 ተማሪዎች በተለያዩ የጤና መስክ አስመረቀ

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 ዓ/ም የተማሪዎችን የምረቃ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክብሯል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ማሙሽ ሁሴን በመረሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎች ለጤና ሥርዓቱ ዋና ድልድይ በመሆን የጤና አገልግሎቶችን ከጤና ተቋማት ወደ ማህበረሰቡ ማድረስ እንዳለባቸው ገልጸዋል። በተለይም…
Read more

በየደረጃው የሚታቀዱ የሕብረተሰብ ጤና ተግባራት ተቀናጀው በመስራት የጤና ስርዓቱን የሚገነቡ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ

የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶችና ጤና ቢሮዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ማናበብ አውደ ጥናት ከነሐሴ 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በተዋረድ በክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች መካከል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በክልሎች የተካሄደውን የእቅድ አፈጻጸም ክትትል እና ግምገማ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ለ2019…
Read more

የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናወነ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ከኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተሮች ኃላፊዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማው መርሃ ግብር መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለጹት፣ የግብ ስምምነቱ ዋና ዓላማ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን በተቀናጀና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም እና የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል ነው። እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዓላማና ራዕይ…
Read more