Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከታዝማ የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና ልዩ ማዕከል ጋር በመተባበር ነፃ የልብ ቀዶ ህክምና መስጠት ጀመረ

CERPHI

ታዝማ ሜዲካል እና ሰርጂካል እስፔሻላይዝድ ማዕከል 11 ለሚሆኑ የልብ ሁሙማን ህፃናት ከሚያዝያ 13 እስከ 18 2018 ዓ/ም ወራቤ ኮምፕረሄንሲቪ ፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዉስጥ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የልብ ቀዶ ህክምና ዘመቻው በዘርፉ ያለውን የወጪ ጫና እና ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገውን እንግልት ከማቃለል ረገድ ሚናዉ የጎላ ነው ብለዋል ።

በክልሉ ይህ ህክምና መሰጠቱ የልብ ህክምና አገልግሎትን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ የገለፁት ሀላፊዉ የህብረተሰቡ የመዳን ተሳፋዉ እንዲያድግ ትልቅ እድል እንደፈጠረላቸው አክለዋል

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የወራቤ ኮ/ስ ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዘይኔ ቢልካ በበኩላቸዉ የወራቤ ኮ/ስ/ሆስፒታል በየምዕራፉ አዳዲስ የጤና ስርዓትን በመዘርጋት ለህብረተሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል

ሆስፒታሉ ነጻ የማህበረሰብ ህክምና ከመስጠት አኳያ ህብረተሰቡን በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውቀዋል ፡፡

‎ሆስፒታሉን የምስራቅ አፍሪካ የጤናው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ በበኩላቸው ‎ከታዝማ ሜዲካል እና ሰርጂካል እስፔሻላይዝድ ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው የልብ ቀዶ ህክምና ለሆስፒታሉም ይሁን ለክልሉ ትልቅ መሰረት የሚጥልና ከፍተኛ ቁርጠኝነት መሆኑንም ዶ/ር ካሊድ አክለው ገልጸዋል ።

የታዝማ ሜዲካል እና ሰርጂካል እስፔሻላይዝድ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ብርሃኑ ሀይለ ማርያም እንደተናገሩት ከሚያዝያ 13 እስከ 18 ባሉት ቀናት ዉስጥ 11 የልብ ሁሙማን ህፃናትን የልብ ቀዶ ህክምና እንደሚደረግላቸው አስረድተዋል ።

ለዚህ ለተቀደሰ ድጋፍና እና ሰብዓዊ ተግባር አቶ ሳሙኤል ለታዝማ ማዕከል ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

‎በማስጀመሪያ መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሞሳ ኤዶሳ፣ የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን እንዲሁም የወራቤ ሆስፒታል የማኔጅመንት አካላትና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *