Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Category: News

CERPHI

የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሮች የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና የኢንስቲትዩትን የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC)፣ የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (VHF) ላቦራቶሪ፣ የጂኖሚክስ ላቦራቶሪ እና የስነ ምግብ ላቦራቶሪዎችን የቴክኒክ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በእውነተኛ ጊዜ ለማስተባበር፣ ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን በሽታ አምጪ ተህዋስያን ለመመርመር፣ የጂኖም ክትትልና ትንተና ለማካሄድ እንዲሁም በስነ ምግብ ዘርፍ የላብራቶሪ ምርመራና ሳይንሳዊ ድጋፍ ለመስጠት ያለውን አቅም ለተሳታፊዎቹ እንዲያውቁ አስችሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የፖሊዮ ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ አቅምን ገመገመ

WHO Delegation Reviews Ethiopia’s Polio Surveillance and Response Efforts የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተገኝቶ ጉብኝቱን ሲያካሂድ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የፖሊዮ በሽታ ክትትል (ቅኝት) እና ምላሽ አሰጣጥ እንቅስቃሴዎችን፣ የላቦራቶሪ የምርመራ አቅምን ለመመልከት እና ኢትዮጵያ ከፖሊዮ ነፃ የሆነችበትን ሁኔታና ደረጃ አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሉ የጋራ ትብብሮችን ለመገምገም እና ለማጠናከር በማለም ነው። በልኡካን ቡድኑ…
Read more

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማና በድግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 202 ተማሪዎች በተለያዩ የጤና መስክ አስመረቀ

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 ዓ/ም የተማሪዎችን የምረቃ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክብሯል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ማሙሽ ሁሴን በመረሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎች ለጤና ሥርዓቱ ዋና ድልድይ በመሆን የጤና አገልግሎቶችን ከጤና ተቋማት ወደ ማህበረሰቡ ማድረስ እንዳለባቸው ገልጸዋል። በተለይም…
Read more

በየደረጃው የሚታቀዱ የሕብረተሰብ ጤና ተግባራት ተቀናጀው በመስራት የጤና ስርዓቱን የሚገነቡ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ

የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶችና ጤና ቢሮዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ማናበብ አውደ ጥናት ከነሐሴ 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በተዋረድ በክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች መካከል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በክልሎች የተካሄደውን የእቅድ አፈጻጸም ክትትል እና ግምገማ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ለ2019…
Read more

የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናወነ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ከኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተሮች ኃላፊዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማው መርሃ ግብር መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለጹት፣ የግብ ስምምነቱ ዋና ዓላማ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን በተቀናጀና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም እና የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል ነው። እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዓላማና ራዕይ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ።

(ሆሳዕና፣ ሐምሌ 25/2018) ኢንስቲትዩቱ ይህን የገለጸው በወራቤ ከተማ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል፣ የበሽታ ቅኝትን፣ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችንና የምርምር ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። በአፈጻጸም ወቅት የተገኙ ልምዶች አስተማሪ በመሆናቸውን ገልጸው…
Read more

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስራ ምልከታ አደረጉ

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 15/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስራ ምልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ ሰልጣኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል። በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በኮሌጁ ልዩ ልዩ የስልጠና እና የስራ ክፍሎችን ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‎100ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በአል አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‎ሀምሌ 7/2018ዓ .ም ‎የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች ፣ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ጉልህ አሰተዋጽኦ ላስመዘገበው ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት (EPHI) ለመቶኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ / እንኳን ደስ አላችሁ!! ‎ኢንስቲቱዩቱ በአዋጅ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመወጣት ረገድ ያስመዘገባቸው እና እያስመዘገባቸው ያሉ ድሎች የሀገራችን የጤና ስርዓት…
Read more

በድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ሚያዚያ 28/2018):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች የአደጋ ማስመሰል ምላሽ አሰጣጥ ተግባራዊ ልምምድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሂዷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም እንደገለጹት በድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው…
Read more

የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት, ቅኝትና ምላሽ ስራዎችን በማህበረሰብ ደረጃ ለመተግበር የሚያስችል Community PHEM የተሰኘው ኢኒሸቲቭ ላይ ምክክር ተካሄደ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የCommunity PHEM ኢኒሸቲቭን በማህበተሰብ ደረጃ ለማስፈጸም የሚያስችል የምክክር ውይይት አካሄደ። ውይይቱ ከክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪዎች፣ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ሀላፊዎች እና የጤና ትምህርት እና ተግባቦት ባለሙያዎች ጋር የተካሄደ ሲሆን በማህበረሰብ ደረጃ የድንገተኛ ጤና አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጓል። የኢንስቲትዩቱ…
Read more