Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: August 2026

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የEOC ስብሰባ ተካሄደ::

ኢንስቲትዩቱ የአደጋ ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ባካሄደው ሳምንታዊ ስብሰባውን የህብረተሰብ ጤና ሁኔታ፣ የበሽታ ክትትል፣ መረጃዎችን እና የተወሰዱ የምላሽ እርምጃዎችን ገምግሟል። የEOC ቡድኑ በሳምንታዊ ስብሰባዉ የክልሉን ነባራዊ የጤና ሁኔታ ፣ ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት ሊሆኑ በሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ዙሪያ፣ የበሽታ ስርጭት፣ የተለያዩ ወረርሽኞች፣ሪፖርቶች እና የምላሽ አፈጻጸም ሂደትን ገምግሟል። አቶ በዓሉ በቴቦ የኢንስቲትዩቱ የቅኝት እና…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ።

(ሆሳዕና፣ ሐምሌ 25/2018) ኢንስቲትዩቱ ይህን የገለጸው በወራቤ ከተማ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል፣ የበሽታ ቅኝትን፣ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችንና የምርምር ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። በአፈጻጸም ወቅት የተገኙ ልምዶች አስተማሪ በመሆናቸውን ገልጸው…
Read more

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስራ ምልከታ አደረጉ

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 15/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስራ ምልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ ሰልጣኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል። በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በኮሌጁ ልዩ ልዩ የስልጠና እና የስራ ክፍሎችን ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‎100ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በአል አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‎ሀምሌ 7/2018ዓ .ም ‎የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች ፣ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ጉልህ አሰተዋጽኦ ላስመዘገበው ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት (EPHI) ለመቶኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ / እንኳን ደስ አላችሁ!! ‎ኢንስቲቱዩቱ በአዋጅ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመወጣት ረገድ ያስመዘገባቸው እና እያስመዘገባቸው ያሉ ድሎች የሀገራችን የጤና ስርዓት…
Read more