
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ከኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተሮች ኃላፊዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፊርማው መርሃ ግብር መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለጹት፣ የግብ ስምምነቱ ዋና ዓላማ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን በተቀናጀና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም እና የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል ነው።
እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዓላማና ራዕይ ለማሳካት የጋራ የሥራ ቁርጠኝነትን ማጠናከርና ኢንስቲትዩቱን የላቀ የሕብረተሰብ ጤና ልዕቀት ማዕከል ማድረግ ከዋና ዓላማዎቹ መካከል መሆኑን ገልጸዋል።
በግብ ስምምነቱ ውስጥ በየዘርፉ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ የአፈጻጸም መለኪያዎች፣ የጊዜ ሰሌዳና የተጠያቂነት ሥርዓት በግልጽ ተካተዋል።
በተለይም በአንድ ጤና ፣ PHEOC፣ ፈጣን ምላሽ ቡድን (Rapid Response Team) አደረጃጀትና የምላሽ አቅምን ማጠናከር፣ እንዲሁም የማገገም ሥራዎችን ማሳለጥ በውይይቱ ወቅት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ነበሩ።
የግብ ስምምነቱ ፊርማ እያንዳንዱ ዘርፍ የተሰጠውን ኃላፊነት በወቅቱና በጥራት እንዲያከናውን፣ ውጤት ተኮር የሥራ አፈጻጸምን እንዲያጠናክር እና የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ ዕቅድ በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል።
