Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ።

CERPHI

(ሆሳዕና፣ ሐምሌ 25/2018) ኢንስቲትዩቱ ይህን የገለጸው በወራቤ ከተማ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል፣ የበሽታ ቅኝትን፣ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችንና የምርምር ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

በአፈጻጸም ወቅት የተገኙ ልምዶች አስተማሪ በመሆናቸውን ገልጸው የ2019 በጀት ዓመት ግቦች የሚሳኩት በጋራ ኃላፊነት፣ በተጠያቂነትና በተቀናጀ አሠራር መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በመድረኩ የቀረቡ ሪፖርቶች የኢኒስቲትዩቱን አቅምና በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ውጤቶችን በግልጽ ማሳየታቸውን ገልጸዋል።

በ2019 በጀት ዓመት የበሽታ ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥን፣ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን፣ የምርምርና የመረጃ ሥርዓቶችን የበለጠ ለማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስበው የሪፎርም ስራዎች መጠናከር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ ሪፖርት እና የተለያዩ የምርምር ሥራዎች እንዲሁም የኢኒስቲትዩቱ ዲጂታላይዜሽን ተግባራት ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱም የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የተገኙ ጥንካሬዎችና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ተለይተው ለ2019 በጀት ዓመት የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የ2019 በጀት ዓመት የኢኒስቲትዩቱ ዕቅድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ከተደረገበት በኋላ የ2019 የአፈጻጸም ግቦች ላይ ኢኒስቲትዩቱ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ከዞንና ልዩ ወረዳ የጤና መምሪያና ጽህፈት ቤት ጋር አካሂዷል።

ተሳታፊዎችም የ2019 በጀት ዓመት ግቦችን በተቀናጀ አሠራር ለማሳካት፣ የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከርና የሕዝብ ጤና አገልግሎትን የበለጠ ለማሻሻል የጋራ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የጤና ተቋማት እና አጋር ተቋማት የዕውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።

በዚህም ከዞኖች ጉራጌ ዞን 1ኛ፣ ስልጤ ዞን 2ኛ፣ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን 3ኛ እንዲሁም ከልዩ ወረዳዎች የቀቤና ልዩ ወረዳ 1ኛ በመውጣት የተዘጋጀላቸውን ዋንጫና ሽልማት ወስደዋል።

በጁሲ ጥላሁን

ለተጨማሪ መረጃ ‼️

📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678

📌 በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225

📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/@centralethiopiacommunication…

📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *