Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

CERPHI

(ሆሳዕና፣ሚያዚያ 28/2018):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች የአደጋ ማስመሰል ምላሽ አሰጣጥ ተግባራዊ ልምምድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት

የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም እንደገለጹት በድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ በቅድመ ዝግጅት፣በቅኝት እና ከምላሽ ተግባራት አንጻር ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየቱን ተናግረዋል።

ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተከሰቱ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ላይ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ሲሰራ መቆየቱን አቶ ወልደሰንበት አስታውሰዋል።

በቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም ከማጎልበት ጀምሮ በተለያዩ የጤና ተቋማት ላይ ኢኒሼቲቮች ተቀርጸው ወደ ተግባር መገባቱን ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።

በክልሉ ወባን ጨምሮ የተለዩ የበሽታ ወረርሽኞችን እንዲሁም በስነ ምግብ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን በመለየት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በመረጃዎች ላይ የተመሰረተ የምላሽ ስራ ሲያጋጥም በበጀት፣በሰው ሀይል እና በሎጂስቲክስ የታገዘ የምላሽ ሲሰጥ እንደነበር ዳይሬክተሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በዘርፉ እየተካሔደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ስራ ስኬታማ ለማድረግ የባለ ብዙ መስሪያ ቤቶችን ሚና ማጎልበት ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል።

በአደጋ መከላከል፣በሴቶች፣በግብርና፣በትምህርት፣እንዲሁም በውሃ እና ከሌሎችም ሴክተሮች ጋር በትብብር የተከናወኑ ስራዎችን አቶ ወልደሰንበት ጠቅሰዋል።

በአደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ በተከናወኑ ስራዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል መድረክ ስለመሆኑም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የተግባር ልምምድ ላይ ትኩረት እንደሚደረግም አመላክተዋል።

በክልሉ የድንገተኛ የጤና አደጋዎች የቅድመ ዝግጅት፣የቅኝት እና የምላሽ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መፈተሽ የሚያስችል መድረክ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በተስፋዬ መኮንን

ለተጨማሪ መረጃ ‼️

📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678

📌 በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225

📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/@centralethiopiacommunication…

📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *