
የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 7/2018ዓ .ም
የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች ፣ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ጉልህ አሰተዋጽኦ ላስመዘገበው ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት (EPHI) ለመቶኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ / እንኳን ደስ አላችሁ!!
ኢንስቲቱዩቱ በአዋጅ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመወጣት ረገድ ያስመዘገባቸው እና እያስመዘገባቸው ያሉ ድሎች የሀገራችን የጤና ስርዓት ምሰሶዎች ናቸው፦
1. ወረርሽኝን መከላከልና ምላሽ በመስጠት፦ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን በፖሊዮ ክትባት ተደራሽ በማድረግ፣ የሕዝብ እንቅስቃሴ ካርታን (Population Mobility Map) በመቅረጽና የድንገተኛ አደጋዎች ማዕከላትን (PHEOC) በማጠናከር የወረርሽኝ መከላከል አቅማችንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ይበል የሚያሰኝ ነው።
2. በምርምርና ማስረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ አሰጣጥ ዙርያ፦ ከ14,475 በላይ በጋራ የተከለሱ (peer-reviewed) የምርምር ጽሑፎችን በማሳተምና ብሔራዊ የምግብ ስብጥር ሠንጠረዥን በማዘጋጀት ለጤና ፖሊሲዎቻችን ሳይንሳዊ መሠረት ጥሏል።
3. በላቦራቶሪና መረጃ አስተዳደር፦ የብሔራዊና ክልል ላቦራቶሪዎችን አቅም በማሳደግ፣ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓትን በመዘርጋትና የጤና መረጃዎችን በአንድ ቋት በማደራጀት ረገድ አኩሪ ውጤት አስመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ባለፉት 100 ዓመታት የተጓዘበት ረጅም ምዕራፍ ፤ የሀገራችንን ሕብረተሰብ ከወርሸኝ ለመጠበቅ፣ የህብረተሰቡን የጤና ችግር በምርምር በመፍታት፣ እና ወረርሽኞች ሲከሰቱ የወረርሽኞችን መንስኤ በላቀ የላቦራቶሪ ምርመራ በማረጋገጥ ያበረከተው አሰተዋጽኦ ታርካዊ ነው።
ይህ የኢንስቲትዩቱ የመቶ ዓመት ታርካዊ ጉዞ የአገራችንን ህዝቦች ሁለንተናዊ ጤና ለማረጋገጥ እና በርካታ ስራዎችን በመስራት የአሀጉሩ የልህቀት ማዕከል (Center of Exellence) በመሆን በትጋት እየሰራ የቆየ ተቋም ነው።
ለመላው የኢንስቲትዩቱ አመራሮች ፣ የድንገተኛ አደጋ ቅኝትና ቁጥጥር፣ የምርምር፣የላቦራቶሪ እና፣የመረጃ ትንተናና ቀመራ ባለሙያዎች እና ለአጠቃላይ ሠራተኞች፦ እንኳን ለ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ !
አቶ ማሙሽ ሁሴን
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
ዳይሬክተር ጀነራል
የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ነፃ የስልክ መስመር፡ 6427
Web site:https://www.cerphi.gov.et
Facebook: https://www.facebook.com/share/p/1EhCBywwTK/
