Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት, ቅኝትና ምላሽ ስራዎችን በማህበረሰብ ደረጃ ለመተግበር የሚያስችል Community PHEM የተሰኘው ኢኒሸቲቭ ላይ ምክክር ተካሄደ

CERPHI

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የCommunity PHEM ኢኒሸቲቭን በማህበተሰብ ደረጃ ለማስፈጸም የሚያስችል የምክክር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ ከክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪዎች፣ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ሀላፊዎች እና የጤና ትምህርት እና ተግባቦት ባለሙያዎች ጋር የተካሄደ ሲሆን በማህበረሰብ ደረጃ የድንገተኛ ጤና አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጓል።

የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በመርሀግብሩ ላይ ኢኒሼቲቩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ ኢኒሸቲቭ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ከማህበረሰብ ጀምሮ በቀላሉ ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የበሽታ ቅኝት ስርዓትን ማጠናከር እና የባለሙያዎችን አቅም መገንባት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። እንዲሁም ከዚህ ቀደም ሲተገበር ከነበረው የጤና ኤክስቴንሽን መርሀግብር ጋር ተባብሮ እና አቀናጅቶ መስራት ለሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች ስኬት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የጤናሚኒስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ እስራኤል አታሮ በበኩላቸው ማህበረሰብ ተኮር አቀራረብ በድንገተኛ ጤና አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ላይ ያለውን ወሳኝ ሚና በመግለጽ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በዚህ ሂደት ውስጥ ቁልፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ ህብረተሰብ ጤና አደጋ ዝግጁነት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ነኢማ ዘይኑ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጹት የCommunity PHEM ኢኒሼቲቭ በማህበረሰብ ደረጃ ያለውን የአደጋ መለየትና ፈጣን ምላሽ አቅም ለማጎልበት ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል።

የኢንስቲትዩቱ የፈጣን ምላሽ ቡድን አስተዳደር ዲቪዥን ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አስራት ይህ የCommunity PHEM ስለሚኖው የአተገባበር ሂደትን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ፍሬምወርክ(Framework) በማቅረብ ስለቀጣይ ስራዎች፣ የአፈፃፀም ሂደት እና የስራ ድርሻዎችን በዝርዝር አስረድተዋል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎች የCommunity PHEM ኢኒሼቲቭን በክልል፣ በወረዳ እና በጤና ኬላ ደረጃ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የተቀናጁ የስራ አቅጣጫዎችን ማካተቱን እና የማህበረሰብ አቅም ማጎልበት፣ የመረጃ ስርዓት ማሻሻል እና ትብብር ማጠናከር እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *