
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 28ኛውን ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ በማስመልከት የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጤናው ዘርፍ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት የመስክ ምልከታ እያደረጉ ነው
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት የጤና ኤክስቴንሽን ስርዓቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል።
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ህዝቡን ለማገልገል በሚደረገዉ ጥረት ተጨማሪ አቅም መሆናቸውን ዶ/ር መቅደስ አብራርተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ስኬታማ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በአዲሱ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ መሰረት የጤና ተቋማት ግንባታ እና ግብአት አቅርቦት ላይ እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ ሳሙኤል አስታውቀዋል።
በክልሉ በህብረተሰብ ተሳትፎ ልዩ ልዩ ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት መቻላቸውን ኃላፊው ጠቅሰዋል።
የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ለመጠበቅ በህብረተሰብ ተሳትፎ የአልትራ ሳውንድ አቅርቦት ማሳደግ ተችሏል ሲሉም ጠቅሰዋል።
በክልሉ የሚካሄደው 28ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ መልካም ልምዶቻችንን የምናካፍልበት ጉድለቶቻችንን ደግሞ የምናርምበት ነው ሲሉም ኃላፊው አብራርተዋል።
Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau




