Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ለሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ የሚውል የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ከዓለም ጤና ድርጅት(WHO) በድጋፍ ተቀበለ፤

CERPHI

‎ቢሮዉ ከዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization) በ60 ሚሊዮን 59 ሺህ 112 ብር የሚገመት የተለያዩ መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ ተቀብሏል።

ድጋፉ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለማከም፣ ለተወሳሰበ የምግብ እጥረት ለተጋለጡ ሕፃናት የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን እንዲሁም ለኮሌራና መሰል በሽታዎች ምላሽ የሚውሉ ግብዓቶችን ያካትታል።

‎በርክክቡ ወቅት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብድልዋሪስ ጀማል እንደተናገሩት ክልሉን ከወረርሽኞችና ከተለያዩ የጤና ስጋቶች ለመከላከል በርካታ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎በክልሉ ጠንካራ የወረርሽን እና ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነት፤ ክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች በመከናወናቸው፣ ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የወባ በሽታ ስርጭትና ጫና መቀነሱን ገልጸዋል።

‎በተለይም ወረርሽኞችን መቋቋም የሚችል ጠንካራ የጤና ሥርዓት በመገንባት ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል።

‎ዛሬ ከዓለም ጤና ድርጅት የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ድጋፍ የክልሉን የጤና ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር፣ የወባ ወረርሽኝንና የተወሳሰበ የምግብ እጥረትን ለመከላከል እንዲሁም ለዜጎች ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አቶ አብድልዋሪስ ጀማል ገልጸዋል።

‎ዋና ዳይሬክተሩ ግብዓቶቹ በቀጣይ ጊዜያት ለታችኛው መዋቅር እንደሚወርድ ገልጸው ለድጋፉ የዓለም ጤና ድርጅትን ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይም የትብብርና የድጋፍ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪአቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *