Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የEOC ስብሰባ አካሄደ ፡፡

CERPHI

ኢንስቲትዩቱ የአደጋ ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ሳምንታዊ ስብሰባውን በማካሄድ በክልሉ የሚገኘውን ነባራዊ የህብረተሰብ ጤና ሁኔታ፣ የበሽታ ክትትልና ቅኝት፣ የወረርሽኝ ሁኔታ እንዲሁም የተወሰዱ የምላሽ እርምጃዎችን ገምግሟል።

የEOC ቡድኑ በሳምንታዊ ስብሰባው የክልሉ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ፣ ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች፣ የበሽታ ስርጭት፣ የተለያዩ ወረርሽኞች፣ ሪፖርቶችና የምላሽ አፈጻጸም ገምግመዋል።

የኢንስቲትዩቱ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሳህሌ ክብሩ መድረኩን በመሩበት ወቅት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የወባ ስርጭት ለመቆጣጠር በተከናወኑ ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች በሳምንቱ የወባ ጫና መቀነሱን ገልጾ ነገር ግን የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች መጠናከር እንደለበት ገልጿል ።

በተጨማሪም የወባ ተጠርጣሪዎችን በአግባቡ ለይቶ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በጤና ተቋማት የሚከናወኑ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሥርዓተ-ምግብ ጫና ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ህፃናት በምግብ እጥረት እንዳይጎዱ በቅንጅት መሥራት፣ ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ጫና ለመቀነስ የልየታና የክትትል ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ በስብሰባው ተነስቷል።

በመድረኩ በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተገምግመው፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *