Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በጤናው ዘርፍ የተደረጉ ድጋፋዊ ክትትሎች የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጣጥ ችግሮች እንዲፈታ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ ፡፡

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ለተከታታይ አራት ቀናት በክልሉ የጤና ልማት ስራዎች ጉብኝት መካሄድ ጀመረ ፡፡

በክልሉ በሀዲያ ዞን በተጀመረው የመጀመሪያ ቀን ጉብኝት በዞኑ ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ሹርሞ ጤና ጣቢያ ፣ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ የሆሳዕና ጤና ጣቢያ እንዲሁም ሆሳዕና ሞዴል ማህበረሰብ መድሃኒት ቤት ተዘዘዋውረው ጉብኝት አካሂደዋል ፡፡

በጤና ተቋማቱ በተደረገው ጉብኝት የጤና ተቋማት አገልግሎት ማሻሻል ፣ ማስፋፋት እና ማዘመን ፣ የህክምና ግብዓት እና መድሃኒት አቅርቦት ፣ የጤና ዘርፍ ማዘመን ፣ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሀድ የደረሰበት ደረጃ ተዘዋውረው ጉብኝት ተደርጓል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በየደረጃው በሚደረጉ ድጋፋዊ ክትትሎች የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ግብዓት ማሟላት የተቋማት ግንባታ ማስፋፋት አሰጣጥ እንዲሻሻል ማገዙን በጉብኝቱ መመልከታቸውን ገልጸዋል ፡፡

እንደ ክልል የሪፈራል ማዕከላትን በክላስተር በማጠናከር ከክልሉ ውጪ ለህክምና የሚደረግ ሪፈርን ለማስቀረት ታቅዶ እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ጠቁመዋል ፡፡

የጉብኝቱ አላማ በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት እንዲሁም ውጤታማ ስራዎችን ለማስፋት መሆኑን ጠቅሰው በባለፈው ጉብኝት የነበሩ ችግሮች መፈታታቸውን ገልጸው የዚህ ጉብኝት አላማም በ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ጥራት ያለው እና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ላይ ለሚሰራው ስራ አጋዥ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

በጉብኝቱ የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ማኔጅመንት ፣ የሌሞ ወረዳ እና የሆሳዕና ከተማ ጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት ተገኝተዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *