Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ዙሪያ ከመዋቅሮች ጋር በበይነ መረብ ዉይይት ተደረገ

CERPHI

የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ የጤናና ጤና ነክ ድን/ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ለህብረተሰቡ ጤና ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሳምንታዊ አፈጻጸም ዙሪያ በዞኑ ሥር ካሉ መዋቅሮች የዘርፉ ባለሞያዎች ጋር በበይነመረብ በዛሬው ዕለት የጋራ ዉይይት አካሂዷል፡፡

በዉይይቱም በዋናነት ቀደም ሲል ባሉት ሳምንታት በዞኑ የወባ ሥርጭት ጫና በጨመረባቸዉ መዋቅሮች በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከባለፈው ሳምንት ቢቀንስም ነገር ግን በሁሉም የጤና ተቋማት ደረጃ በተለይ በጤና ኬላዎች የወባ ምርመራ ሽፋን ዝቅተኛ መሆኑን፣የወባ በሽታ ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሰዎች ወባ በሽታ የመገኘት ምጣኔ (Positivity rate) ከፍተኛ መሆኑን የተገመገመ ሲሆን የወባ መከላከል ቁጥጥር ስራዎችን በየደረጃዉ አጠናክሮ ማስቀጠል፣በወባ መከላከልና ማስወገድ የማህበረሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎን ማጠናከር፣የወባ ምርመራ እና የህክምና ግብአቶችን በሁሉም ጤና ተቋማት ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ፣የክትትልና ግምገማ ሥርዓቱን በየደረጃው ማጠናከር እንዲሁም የወባ በሽታ ቅኝትና ምላሽ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል የቀጥይ ቀናት የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *