Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ኢኖቬሽን ኔትወርክ መደበኛ የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል

የጤና ኢኖቬሽን ኔትወርክ ዋና ዓላማ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ ኢኖቬሽኖች ከሃሳብ እስከ ትግበራ በማሸጋገር የሕክምና አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ማሻሻል ነው።

ይህ ኔትወርክ ዋና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር ተዋናይ በሆኑት የፈጠራ ባለቤቶች፣ በተመራማሪዎች፣ በጤና ባለሙያዎች፣ በመንግስትና በግል ባለሀብቶች መካከል መቀራረብና መግባባትን በመፍጠር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢን በመፍጠር ውጤታማ የሆኑ የኢኖቬሽን ስራዎች ጥራትና ደህንነታቸዉ በተረጋገጠ ሁኔታ በፍጥነት ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በመርሃ ግበሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃርላ አብዱላሂ እንደተናገሩት የኢኖቬሽን ኔትወርክ ጠንካራ የጤና ኢኖቬሽን ሥነ-ምህዳርን ለመገንባት ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዉ ለጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት መሻሻል ኢኖቬሽን የሚኖረዉን ሚና በሚገባ ለመጠቀም ሁሉም የኢኖቬሽን ሥነ-ምህዳር ተዋናዮች ድርሻቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም ባለፈው ዓመት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ (Global Innovation & Quality Summit 2025) ላይ በክብርት ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቀረበው “የኢኖቬሽን ጥሪ” (Call for Innovation) መነሻነት ከቀረቡት ከ50 በላይ የኢኖቬሽን ሃሳቦች ለመጨረሻ ደረጃ የደረሱ 10 ኢኖቬሽኖች ቀርበው በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ዳኞች አስተያየት የተሰጡ ሲሆን ጤና ሚኒስቴር እነዚህ የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተጠቅሷል፡፡

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *