
የአርማወር ሐንስን የምርምር ኢንስቲትዩት ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር የተጣጣሙና ለአገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በቀጥታ ምላሽ የሚሰጡ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሳይንሳዊ ሥራዎችን ለመደገፍ ተብሎ የተገነባ መሆኑን የጤና ሚኒሰትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ አገራዊ ፖሊሲዎችን እና የሕክምና ልምዶችን የሚደግፉ መረጃዎችን በማመንጨት ረገድ የጤና ምርምር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በአገር ውስጥ የተመሠረቱ የምርምር ተቋማት መኖራቸው ከፍተኛ አስተዋፅዎ አድረገዋል ያሉት ሚኒስትሯ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ክሊኒካዊ ምርምሮችን የማካሄድ ችሎታ እና አገራዊ የጤና ምላሾችን ከመደገፉም በላይ ኢንስቲትዩቱ በዓለም አቀፍ ደረጃም የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም የተመረቀው የአርማወር ሐንስን የምርምር ኢንስቲትዩት ዘመናዊ የምርምር ላብራቶሪ ኮምፕሌክስ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ገለፃ አድርገዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፤ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፤ ከተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶችና ተቋማት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩትን የምርምር ላብራቶሪዎች/ ከባዮሪፖዚቶሪ እስከ ክትባት ምርምር ክፍል/ ፤ የላብራቶሪ እንስሳት ማርቢያና ምርምር ማዕከል፤ የባህል ህክምና ዕፅዋት ጋርደን እና የሶሊድና ሊኩይድ ዌስት ትሪትመንት ፕላንት ተዧዙረው ተመልክተዋል፡፡
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB


