Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በላንፉሮ ወረዳ የወረዳውን የጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በወረዳው መንግስት ከ 35 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ በይፋ ተመረቀ!

CERPHI

ወራቤ፣ ሚያዚያ 24/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን)

በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ የወረዳውን የጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥና የማህበረሰቡን የጤና አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ በወንቴ ሎላ ቀበሌ ከ 35 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የጦራ ከተማ አስተዳደር ከ 3 ሚሊየን ብር በላይ የቁሳቁስና የሰንጋዎች ስጦታ አበርክቷል።

በሌላም በኩል የጦራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ከ181 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ቁሳቁሶችን ለጤና ጣቢያው ማበርከታቸው ታውቋል።

በተያያዘም የሚቶ ወረዳ አስተዳደር የሰንጋዎች ስጦታ በማበርከት ለወረዳው ልማት አጋርነቱን ማሳየቱ ተመላክቷል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን፣ የስልጤ ዞን አስተባባሪ አካላት እና ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የላንፉሮ ወረዳና የጦራ ከተማ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *