Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Category: News

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

በአፈጻጸም ግምገማው ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች አፈጻጸማቸውን አቅርበው ውይይት ተካሂዷል ፡፡ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመድረኩ እንደገለጹት ባለፉት 6 ወራት በኢኒስቲትዩቱ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም አበረታች እና ውጤታማ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ የተሻለ ለመፈጸም የሚያነሳሳ ስለመሆኑም አስረድተዋል። የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው የጤና አገልግሎት ስርዓቱን በመገንባት በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በአፋጣኝ…
Read more

በክልሉ ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለጤና መረጃ ሰብሳብዎች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በጤና ተቋማት ውስጥ የተገልጋዮች እርካታ መጠን ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመለየት ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል። ሰልጣኞቹ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች (ከዋቸሞ፣ ከወራቤና ወልቂጤ) እንዲሁም ከሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተውጣጡ ተመራማሪዎችና መምህራን ናቸው። በክልሉ ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የተገልጋዮች እርካታ መጠን ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት…
Read more

የፓን-አፍሪካ የቀዶ ህክምና የጤና እንክብካቤ ፎረም መካሄድ ጀመረ::

የፓን-አፍሪካ የቀዶ ህክምና የጤና እንክብካቤ መድረክ በአዲስ አበባ የተከፈተው “ከፖሊሲ ወደ ተግባር፡ የአፍሪካን ባለብዙ ዘርፍ የቀዶ ህክምና የሰው ኃይል ማስፋት” በሚል መሪ ቃል ነው። ዓለም አቀፍ ስብሰባው በአፍሪካ የቀዶ ህክምና እንክብካቤ ስርዓቶችን ለማጠናከር መንገዶችን ለማመቻቸት ከመላው አህጉር የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮችን፣ የህክምና ባለሙያዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና ዓለም አቀፍ የጤና አጋሮችን አሰባስቧል። ፎረሙ አባል ሃገራት ልምድ የሚለዋወጡበት እና…
Read more

የአእምሮ ጤና አገልግሎትን በድንገተኛና በከፍተኛ አደጋዎች ወቅት ተደራሽ እናድርግ!” በሚል መሪ ቃል የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ተከበረ::

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎችና የማናጅመንት አካላት የዞንና የልዩ ወረዳ ጤና መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች የሆስፒታሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “የአእምሮ ጤና አገልግሎትን በድንገተኛና በከፍተኛ አደጋዎች ወቅት ተደራሽ እናድርግ!”በሚል መሪ ቃል የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በዛሬው ዕለት ተከብሯል። አቶ ለገሰ ጴጥሮ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት…
Read more

የየም ባህል መድኃኒት እውቀት እና አጠቃቀም ዙሪያ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት እና የባህል መድኃኒት ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀመረ ።

በመድረኩ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማሀዲ፦ በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ስፖርት ሚንስትር ደኤታ፣ ፕሮፈሰር አፈወርቅ ካሱ ፦ የአርማወ አንሰን የጤና ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ አበራ ስዩም፦ የኢትዮጵያ ብዝሀ ኢንስቲትዩት ተቋም ተወካይ፣ አቶ ሙሉቀን ፈሊጶስ፦ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋም ተወካይ፣ አብርሀም መጫ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደንና አከባቢ ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ፣ የአረሚያ ዩኒቨርስቲ ፣…
Read more

በክልሉ የሚገኙ ስድስት የንቅናቄ ተቋማት የስራ አፈጻጸም በዱራሜ ከተማ ተገመገመ::

(‎ሆሳዕና፦ጥቅምት 14/2018)፣ ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ስድስት የንቅናቄ ተቋማት አፈጻጸም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች በተገኙበት በዱራሜ ከተማ ተገምግሟል።‎የግምገማ መድረኩን የመሩት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይሁን አሰፋና የጽህፈት ቤቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ ናቸው።‎ ‎በመድረኩ ጤና፣ገቢ፣ንግድና ገበያ ልማት፣ግብርና፣‎ምግብ ዋስትና እና ስራ ዕድል ፈጠራ…
Read more

የህብረተሰቡን የጤና ስርዓት መገንባት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል አቶ ማሙሽ ሁሴን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር::

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ/ም ዓመታዊና የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል የክልሉ ጤና ቢሮ ምክ/ሀላፊና የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለፁት የህብረተሰቡን የጤና ስርዓት መገንባት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱን…
Read more

ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ፈጣን ፣ ጥራት ያለው እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ስርዓት ለመገንባት እየሰራ መሆኑን የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ ፡፡

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ለወረዳዎች ታብሌት ድጋፍ አደረገ:- ጥቅምት 10/2018:- ቁሊቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ያበረከታቸው ታብሌቶችን በዛሬው ዕለት ለወረዳዎች አስረክቧል ። ዶ/ር ሸምሱ ረሽድ ባደረጉ የመክፈቻ ንግግር ለድንገተኛ ወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት በመገንባት በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞች በማህበረሰቡ ላይ የከፋ የጤና ጉዳት አንዳያደርሱ በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ የጤና አገ/ት ለሁሉም…
Read more

ዓለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ::

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዓለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት (ጋቪ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳኒያ ኒሽታር (ዶ/ር) ጋር በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ካለው የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል። በውይይታቸውም የጤና ስርዓት ላይ ያለውን ትብብርን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ አቶ አህመድ ሽዴ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እያደረገ ያለውን የረጅም ጊዜ ድጋፍ…
Read more

ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ፈጣን ፣ ጥራት ያለው እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ስርዓት ለመገንባት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች ላፕቶፕ እና ታብሌት ድጋፍ አደረገ ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ካበረከታቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች 85 ታብሌቶችና 10 ላፕቶፖች በዛሬው ዕለት ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አስረክቧል ። አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር…
Read more