Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

CERPHI

በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደበኛ የወረርሽኞች መቆጣጠሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center – EOC) የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ሳምንት ( WHO weeke 10 ) ግምገማ በቀን 11/07/2016 ዓ/ም ባደረገው ውይይት በክልሉ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደገለጹት ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጠናከር አንጻር መንግስታዊ ያልሆኑ የጤና ልማት ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሳምንታዊ የወረርሽኞች ግምገማ (EOC) ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ሁሉንም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን ያካተተ ሳምንታዊ የበይነ መረብ የወረርሽኞች ግምገማ ሊጀመር እንደሚገባም ገልጸዋል፡

በውይይቱም የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞትን ከመቀነስ አንጻር ሞትን በሪፖርት ከማሳወቅ ጀምሮ የሞት ኦዲት ተሰርቶ የመከላከል ስራዎች መሰራት እነብዳለባቸው የተጠቆመ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ወሳኝ መሆናቸውም ተገልጾአል፡፡

የወባ በሽታ በሳምቱ የመጨመር አዝማሚያ የታየበት ሁኔታ መኖሩ የተጠቆመ ሲሆን በተለይም በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ፤ በዓለም ገበያ እና በወልቂጤ ከተሞች የአካባቢ ቁጥጥርን ጨምሮ የመከላል እና የመቆጣጠር ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ከፍተኛ እና መካከለኛ የምግብ እጥረት በተመለከተ ከልየታ ጀምሮ የህክምና ጥራት ላይ ትኩረት በመስጠት፣ የማጅራት ገትር በሽታ ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የሰርቬላንስ ስራዎች በማጠናከር፣ በጤና ተቋማት የሚሰጡ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡን በማሳለጥ፣ የፈጣን ላቦራቶሪ ምርመራ ኪቶች የማቅረብ ስራ ሊሰራ ይገባልም ተብሏል።

የኩፍኝ ወረርሽኝን በተመለከተ በክልሉ አብዛኛዎቹ መዋቅሮች የኩፍኝ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሰርቬላንስ ፤ የክትባት እና የህክምና ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ከኮሌራ ወረርሽኝ ቁጥጥርና መከላከል አንጻር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መተግበር ይገባልም ተብሏል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *