Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

” የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር በጤና ተቋማት ደረጃ (Public Health Emergency Management at Health Facility) ትግበራን ማጠናከር አስተማማኝ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የመከላልና የመቆጣጠር ስርዓት ለመገንባት እንደሚያስችል ተገለጸ።

CERPHI

” የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር በጤና ተቋማት ደረጃ (Public Health Emergency Management at Health Facility) ትግበራን ማጠናከር አስተማማኝ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የመከላልና የመቆጣጠር ስርዓት ለመገንባት እንደሚያስችል ተገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት ጋር በመተባበር በቡታጅራ ከተማ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር በጤና ተቋማት (PHEM at Health Facility) ስልጠና አዘጋጅተዋል።

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና አንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የመልሶ ማቋቋምና ሪዚሊየንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክር ዶ/ር በላይ ማካንጎ እንደገለጹት የስልጠናው አላማ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሲከሰቱ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የጤና ተቋማት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል።

እንደ ሀገር በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ሆስፒታሎች የተጀመረው ይህ የሙከራ ትግበራ በማሕበረሰብ ደረጃ የሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን ቀድሞ በመለየት በአግባቡ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል እና ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የገለጹት ዶ/ር በላይ ፕሮግራሙን የበለጠ ለማጠናከር በቀጣይ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ስልጠና በክልሉ የተጀመረውን የሙከራ ትግበራ ውጤታማ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም በበኩላቸው የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር በጤና ተቋማት (PHEM at Health Facility) ትግበራ ማጠናከር አስተማማኝ የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን የመከላልና የመቆጣጠር ስርዓት ለመገንባት የተያዘውን ስልታዊ ዕቅድ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

የጤና ተቋማት የጤና መረጃዎችን ቀጥታ ከማሕበረሰቡ የሚያገኙ በመሆናቸው የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ተግባራት በትክክለኛ የአሰራር ስርዓት ፤ በሚፈለገው ጥራት እና በተቀመጠላቸው ሳይንሳዊ የጊዜ ቀመር በመሰብሰብ ፤ በመተንተን እና ለውሳኔ በመጠቀም በማሕበረሰብ ደረጃ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና አደጋዎችን መከላከል እንደሚገባ እና የተጀመረው ትግበራ ውጤታማ በመሆኑ በሌሎችም ሆስፒታሎች ለማስቀጠል ጥረት እንደሚደረግ አቶ ወልደሰንበት አክለው ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በፓይለት ፕሮግራም የተመረጡ የስድስት መሪ ሆስፒታሎች የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መቆጣጠር ኦፊሰሮች ፤ የድንገተኛ አደጋ ክፍል አስተባባሪዎች እና የጥራት ኦፊሰሮች እንዲሁም ሆስፒታሎቹ የሚገኙባቸው ዞኖች የዳይሬክቶሬቱ አስተባባሪዎች የስልጠናው ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *