Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች 100 ሚሊዮን የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

CERPHI

ድጋፉም፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ከክልሉ መንግስት ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በግዢ እና በድጋፍ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት ባለፉት አመታት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን መጠነ-ሰፊ ሥራዎች ተሰርቷል።

በዚህም በጤናው ዘርፍ የመጡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የተደረገው ድጋፍ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ለታለመለት ዓላማ ልውል እንደሚገባ አሳስበዋል አቶ ሳሙኤል።

በተለይ የክትባት ፕሮግራም ተደራሽነት ለማስፋት፣የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥራዎችን ለማዘመን፣ የጤና ቁጥጥር ሥራዎችን ለማቀላጠፍና ለጽዱ ኢትዮጵያ አተገባበር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በክልሉ የጤናው ዘርፍ ለማዘመን አገልግሎት ለማሻሻል የተደረጉ ሀብቶች ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲውሉ አቶ ሳሙኤል ጠቁመዋል ፡፡

በወቅቱም 18 ሞተር ሳይክል ፣ 188 ኮምፒዩተርና 133 ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ለጽዱ ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ ግብዓቶች ስርጭት ለመዋቅሮቹ ተደርጓል።

የዞን እና ልዩ ወረዳ ጤና ኃላፊዎች ከክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፣ ከምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ርክክብ አድርገዋል ፡፡

አብርሃም ሙጎሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *