Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የወባ በሽታ መከላከል ስራችን የተቀናጀ ትኩረት የሚፈልግ ነው አሉ የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን

CERPHI

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የበሽታ መከላከል ጤና ማጎልበት ዋና የስራ ሂደት የ9 ወር አፈጻጸም ግምገማ እና በቀሪ ወራት ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ወራቤ ፣ሚያዝያ 14/2018 ፣ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን የወባ በሽታ መከላከል ዘርፍ ላይ በየጊዜው በተፈጠሩ ስልጠናዎችና የንቅናቄ ስራዎች ውጤታማ ሊባል በሚችል መልኩ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግበናል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ37 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በዞኑ በርካታ ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የገለጹት አቶ ሸምሱ አሁንም የወባ በሽታ መከላከል ስራችን የተቀናጀ ትኩረት የሚፈልግ ነው ብለዋል፡፡

በሽታውን በዘላቂነት ለመከላከል የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አቶ ሸምሱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ሸምሱ አክለውም የቲቢ በሽታ በመከላከል ረገድ ሰፊ ክፍተቶች መኖራቸውን በመጥቀስ በሽታውን የመለየትና የመከታተል ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣የሆስፒታልና የጤና ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *