
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመረቀውና በዓይነቱ ልዩ የሆነው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) አዲሱ ላቦራቶሪ ኮምፕሌክስ በሠራተኞችና በእንግዶች ተጎበኘ።
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ከ20 ሠራተኞች ተነስቶ ዛሬ ከ700 በላይ ባለሙያዎችን የያዘ ግዙፍ የሳይንስ ማዕከል ሆኗል። ማዕከሉ ሀገር በቀል እውቀትን ወደ ላቀ ሳይንሳዊ ምርምር በማሸጋገር የሀገራችንን የጤና ደኅንነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው።
በዕለቱም ለተቋሙ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትና ለአለርት ኮሞፐሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።





