Our currenct vacancies
የክልሉ ሕ/ጤ/ኢ/ የመረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ከኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሔራዊ የመረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ጋር በመተባበር ´”ብሔራዊ የጤና መረጃ መለኪያ ስርዓት ለተሻለ ውሳኔ (Health-MIND)“ በሚል ርዕስ ለሚተገብረው አገር አቀፍ ፕሮጅከት በቁጥር 69/167 በቀን 24/2018 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ በክልላችን ውስጥ በእጣ በተመረጡ ወረዳዎች መረጃ በመሰብሰብና የድጋፍና ክትትል ስራ የሚሰሩ ባለሙያዎችን ቀጥሎ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ባለሙያዎች ከስር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማስረጃችሁን ማያያዝ እና ማስገባተ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተያያዥ ለሆኑ ጉዳዮች 1.አቶ ሳሙኤል ሀይሉ ስልክ +251946468531 እንዲሁም አቶ አዲሱ ቸርነትን ስልክ 0916076784 በመደወል ሚገጥማችሁን ችግር ማሳወቅ ትችላላችሁ።
የመረጃ የሚሰበሰብባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ዝረዝር
| ተ ቁ | አከባቢ | ክልል | ዞን | ወረዳ | ቀበሌ |
| 1 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ሀድያ | ምስራቅ ባደዋቾ | አንደኛ ጨፋ |
| 2 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ሀድያ | ሚሻ | ዲልባራ |
| 3 | ከተማ | ማ/ኢ/ክ | ምስራቅ ጉራጌ | መስቃን | ዶቢ |
| 4 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ስልጤ | ምእራብ አዘርነት | ቢላሎ |
| 5 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ስልጤ | ሁልባረግ | ደመቄ |
| 6 | ከተማ | ማ/ኢ/ክ | ስልጤ | ወራቤ ከተማ አስተዳደር | ወራቤ 01 |
| 7 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ጉራጌ | እኖር ኢነር መገር | ይባረኘ |
| 8 | ገጥር | ማ/ኢ/ክ | ጉራጌ | እዣ | ቀራተሞ |
| ተ.ቁ | የስራ መደብ መጠሪያ | አስፈላጊ የትምህርት ደረጃ | አስፈላጊ ቁጥር | አስፈላጊ መስፈርት | የስራ ልምድ | አስተያየት |
| 1. 2. | የመረጃ ሰብሳቢ ሠራተኛ/Data collector/ | BSc/BA እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት ወይም ከዚያ በላይ | 8 | መረጃው በሚሰበሰብባቸው ቀበለሌዎች ነዋሪ የሆነ የአካባቢ ቋንቋ እና ባህል እውቀት ያለው | መረጃ በመሰብሰብ ልምድ ያለው (ቢያንስ አንድ ልምድ) | የወረዳው ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ |
| የመስክ አስተባባሪ /Field supervisors/ | BSc/BA እና ከዚያ በላይ ያለው በማንኛውም የትምህርት መስክ ያለው/ያላት እና ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ ያለው | 2 | መረጃው በሚሰበሰብባቸው ቀበሌዎች አካባቢ ነዋሪ የሆነ በቤተሰብ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም በሕዝብ ጤና ምርምር በመረጃ መሰብሰብ ወይም መረጃ አሰባሰብ ልምድ ያለው/ያላት | በአካባቢያዊ ወይም በብሔራዊ ጥናቶች መረጃ አሰባሰብ ላይ ልምድ ያለው/ያላት | የወረዳው ወይም ዞን ወይም ከልል ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ |
| ተ.ቁ | የስራ መደብ መጠሪያ | የስራ ድርሻ/ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች |
| 1 | የመረጃ ሰብሳቢ ሠራተኛ/Data collector/ | የመረጃ አሰባብሰብ ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን ፈቃድኛነታችውን ያረጋግጣል፣ ስለ መረጃው ዓላማ እና ጥቅም ያስረዳል። የመረጃ አሰባሰብ እንቅስቃሴዎችን እና መርሃግብሮችን ያቅዳሉ፤ በቀጣይነት ስራዉን ይሰራሉየመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን በሚስጥር ያስቀምጣሉ እንዲሁም ይጠብቃሉ።ትክክለኛውን የመረጃ መሰብሰቢያ ግባትን በመጠቀም መረጃውን በጥራትና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ይሰበስባልበየቀኑ የተሰበሰቡ መረጃወችንና ያጋጠሙ ችግሮችን፣ ለመስክ አስተባባሪው ሪፖርት ያደርጋል/ያስተላልፋልመልካም ተሞክሮዎችን ይቀምራሉ እንዲሁም ለመስክ አስተባባሪ ሪፖርት ያቀርባሉ።የመረጃ አሰባሰብ ስራ የሚያካለለዉን ቦታ እና የመረጃ ሰጭ አካልትን ይለያሉበተመደበው ቀበሌ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የቤተሰብ አባላት በክትትል ወቅት በታማኝነት ይካልላልየሚሰበሰበውን የመረጃ ጥራት ይግመግማል፤ያረጋግጣል፣ የተሰበሰበውን መረጃ ሙሉነት ያረጋግጣል።መረጃ አሰባሰብ ወይም የሚቀርቡ እቅዶችን ተግባራዊ ያደርጋሉ እንዲሁም ያክብራሉ።በተመደበበት ቀበሌ የሚፈጠሩ የማህበረሰብ ክስተቶችን ይከታተላል፣ ሪፖርት ያደርጋል። እየተካሄደ ባለው የመረጃ አሰባሰብ አግባብነት እና አስፈላጊነት ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ይፈጥራልበክልልዊ ስብሰባዎች ወይም ውይይቶች ላይ ሊሳተፍ ይችላልከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተቀናጅቶና ተግባብቶ ይሰራል በመረጃው አሰባሰብ መመሪያ መሰረት መረጃን ይሰበስባል |
ተቁ | የስራ መደብ መጠሪያ | የስራ ድርሻ/ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች |
| 2. | የመስክ አስተባባሪ /Field supervisor/ | ለመረጃ ስብሰባ ስራ የሚውሉበት/የቀን ውሎ ካርታ ወይም እቅድ ያወጣል እንዲሁም ይተገብራል።መረጃ ሰብሳቢዎቸ ይመድባል፣ይቆጣጠራልለክልል አስተባባሪ እስካልነገሩ ድረስ በተመደበው ወይም በሚወለብት/የቀን ውሎ ካርታ መረጃ መሰብሰቢያ ቦታ በማንኛውም ጊዜ መገኘት ይኖርባቸዋል።የቀበሌዎችን የመረጃ አሰባሰብ እንቅስቃሴ ከክልል አስተባባሪ ጋር አቅዶ ይቆጣጠራል እንዲሁም ይሰራል።የመረጃ አሰባብሰብ ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን ፈቃድኛነታችውን ያረጋግጣል እንዲሁም ስለ መረጃው ዓላማ እና ጥቅም ያስረዳል።የግለሰብ እና የቤተሰብ ምስጢሮች እውነተኛነትና እና ሚስጥራዊነትን ይጠብቃል።በድርጊት መርሃ ግብሩ መሰረት የመረጃ ሰብሳቢዎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል።የተሰበሰበውን መረጃ ጥራት ይግመግማል፤ ሙሉነት ፣ ወጥነት እና ተነባቢነት ይገምግማል ያረጋግጣል። እንዲሁም በተገኙ ከፍተቶች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል ፣ ይመክራል።የቤተሰብ/የግለሰብ መለያ ቁጥር ትክክለኛነቱ እና ተዛማጅነቱን ያረጋግጣልየተሰበሰቡትን መረጃዎች በየቀኑ ለክልል አስተባባሪ ቢሮ ሪፖርት ያድርጋልየተመደበው የመረጃ ሰብሳቢ ባለሙያው ያለምክኒያት ሦስት ቀን ከስራ ገበታው ከቀረ ወይም ከጠፋ ለክልል አስተባባሪ ሪፖርት ያደርጋል።በሌላ መተካት ያለበትን የመረጃ ሰብሳቢ በፍጥነት እንዲተካ ያስተባብራልየመረጃ አሰባሰቡ ሂደትና አላማን በተመለከተ ለማህበረሰብ/ለአካባቢው ተወካዮች ወይም ሃላፊዎች ያሰርዳል።በጋራ የመስራት እና የቡድን መንፈስን ይጠብቃልበመረጃው አሰባሰብ መመሪያ መሰረት መረጃ መሰብሰቡን ያረጋግጣልለስራው አስፍላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ያውላል። ከክትትል ተግባራት በተጨማሪ፡- መረጃ ሰብሳቢው ከሌለ የመረጃ ሰብሳቢውን ስራዎች እና ሃላፊነት ወክሎ ይሰራል።የመረጃ አሰባብሰብ ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን ፈቃድኛነታችውን ያረጋግጣል ፣ ስለ መረጃው ዓላማ እና ጥቅም ያስረዳል። የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን በሚስጥር ያስቀምጣል እንዲሁም ይጠብቃል።እያንዳንዱ የተሰበሰቡ መረጃዎችን ወይም ተዛማጅ ጉዳዮችን በየቀኑ ለሚመለከተው የመስክ አስተባባሪ ወይም ለክልሉ አስተባባሪ ሪፖርት ያደርጋል፤ በስራ ላያ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና አስቸኳይ ሁኔታዎች ሲያጋጠሙ ለመስክ አስተባባሪ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።መልካም ተሞክሮዎችን ይቀምራሉ እንዲሁም ለክልል አስተባባሪ ቢሮ ሪፖርት ያቀርባሉ።ተመደበው ቀበሌ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የቤተሰብ አባላት በክትትል ወቅት በታማኝነት ያካልላል።በተመደበበት ቀበሌ የሚፈጠሩ የማህበረሰብ ክስተቶችን ይከታተላል፣ ሪፖርት ያደርጋል።እየተካሄደ ባለው የመረጃ አሰባሰብ አግባብነት እና አስፈላጊነት ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ይፈጥራልለተጠየቁት ብሄራዊ/ክልልዊ/ ስብሰባዎች ወይም ውይይቶች ላይ በሰዓቱ ይገገኛሉለስራው አስፍላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እንዲሟሉ ይከታትላል፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋላችውን ይከታተላል። |
