Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ስታርሊንክን በመጠቀም በገጠር የጤና ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋት የሚያስችል ውይይት ከስፔስኤክስ ልዑካን ቡድን ጋር አካሂደዋል።

CERPHI

በስብሰባው የስፔስኤክስ ልዑካን ቡድን ስታርሊንክ በአሁኑ ጊዜ በ169 አገሮች ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎት ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል። አገልግሎቱ በተለይም በሩቅ እና በቂ የኔትወርክ አገልግሎት በማያገኙ አካባቢዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት ለማቅረብ ያለመ ነው።

ስፔስኤክስ በተለይ ለገጠር የጤና ተቋማት የኢንተኔት አገልግሎትን በማቅረብ ረገድ መልካም አማራጭ ማቅረቡን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ብዙ የጤና ተቋማት አሁንም አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እያገኙ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአገሪቱን የዲጂታል የጤና ስርዓት ለማጠናከር ከስፔስኤክስ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ዶ/ር መቅደስ ገልፀዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

See less

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *