
በጤና ዘርፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አጠቃቀምን ለማሳደግ የሚረዳ ውይይት ተካሄደ
__________
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጌትስ ፋውንዴሽን ልዑካን ቡድን ጋር በጤና ዘርፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አጠቃቀምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይት መድረኩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የምርመራ መሳሪያዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ በጤና ስርዓቱ ውስጥ አጠቃቀሙን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ጤና ሚኒስቴር በመላ አገሪቱ የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን ለማሻሻል በሚደረገው ቀጣይ ጥረት በጤናው ዘርፍ የAI አጠቃቀምን ለማሳደግ የአጋር ድርጅቶችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB



