
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና ማስተባበሪያ ማዕከል በወባ በሽታና በሌሎች ወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ ሳምንታዊ የግምገማና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የወባ በሽታ ስርጭት ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በቀጣይ የወባ በሽታ ጫናን በዘላቂነት ለመቀነስ፦
የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር፣ የአጎበር አጠቃቀምን ማሳደግ፣ የግብዓት አቅርቦትና ቁጥጥርን ማረጋገጥ፣የወባ ምርመራ አገልግሎት ጥራትን ማስጠበቅ ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ወባ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ሆኖ እንዳይሆን የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ
እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ውጤታማነት መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት መስጠትና መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል።
የወባ መከላከያ ግብዓቶች ለታችኛው መዋቅር መድረሳቸውን ማረጋገጥ፣ የቲቢ (TB) በሽታ መከላከል ስራን ማጠናከር፣ የኤች አይቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ስርጭትን ለመቀነስ ማህበረሰቡ ከመዘናጋት ወጥቶ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ የግንኙነት ስራዎችን አጎልብቶ ማስቀጠል በሚሉና በሌሎች የጤና ጉዳዮች የውይይት መድረኩ ትኩረት በመስጠት መክሯል።
ዝናሽ ደለለኝ



