Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ሳምንታዊ የህረተሰብ ጤና አደጋዎች ውይይት ተካሄደ ፡፡

ሳምንታዊ የህረተሰብ ጤና አደጋዎች ውይይት ተካሄደ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና ማስተባበሪያ ማዕከል በወባ በሽታና በሌሎች የጤና ጉዳዮች ሳምንታዊ ውይይት አድርጓል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመድረኩ እንደገለጹት የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር በ32% ጭማሪ ማሳየቱን በመጠቆም በቀጣይ ጊዜያት ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ የወባ በሽታ ጫናን በጉልህ ለመቀነስ የሚያስችሉ የአካባቢ ቁጥጥር የአጎበር አጠቃቀም የግብዓት ቁጥጥር እና የወባ ምርመራ አገልግሎት ጥራትን የማስጠበቅ ስራዎች በልዩ ትኩረት መፈጸም እንደሚገባ ተናግረዋል።

ባለፉት ጊዜያት የተሰራው የወባ በሽታን የመከላከሉና የመቆጣጠሩ ስራ ውጤታማ መሻሻል ማሳየቱን ያመላከቱት ዋና ዳይሬክተሩ በሁሉም የክልሉ አካባቢ የተጠናከረ የመከላከል ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ከክልል እስከ ወረዳ በተዋረድ የሚገኙ አመራር አካላት ሁሉ ከዚህ በፊት ሲደረግ የነበረውን የመከላከልና የመቆጣጠር ድጋፍ በማጠናከር መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳሰቡ ሲሆን፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሳምንታዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ውይይት ሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች በሚከሰቱ ሰዓት በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የጤና ስርዓቱን ለወረርሽኝ የማይበገር አድርጎ ለመገንባት አስፈለጊ መሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ማሙሽ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጊዜ እንዴት መስጠት እንደሚቻልና፣ ከህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አድጋዎች በፊት መደረግ ስላለባቸው የዝግጅት ጉዳዮች፣ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የመለየት ሂደት፣በማህብረሰቡ ዘንድ ከሚከሰቱ የጤና አደጋዎች በፊት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች፣በህብረተሰብ አደጋ ወቅት ስለሚሰሩ ስራዎች እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ ስለሚደረጉ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን በስፋት እና በጥልቀት በመፈተሸ የጤና ስርዓቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻሽል የሚያስችል ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ተገቢውን የወባ በሽታ ድጋፍና ክትትል በወቅቱ ማድረግ የወባ በሽታ ግብዓቶች በወቅቱ ወደታች መውረዳቸውን ማረጋገጥ የቲቢ በሽታ መከላከል ስራን ማጠናከር የኤች አይቪ ኤድስ በሽታን አስመልክቶ ማህበረሰቡን ከመዘናጋት ሊያወጣ የሚችል የባህሪ ለውጥና የተግባቦት ስራዎችን አጎልብቶ ማስቀጠል በሚሉ እና በሁሉም የጤና ጉዳዮች የውይይቱ ተሳታፊዎች አጽንኦት ሰጥተው መክረዋል።

ዝናሽ ደለለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *