
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል የመረጃ ሙሉዕነትና ታዓማኒነት ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር መሻሻል የታየበት መሆኑን ገልጸው ይህንኑ ወጤት አጎልብቶ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የወባ በሽታ ጫና ያለባቸውን የክልሉ አካባቢዎች በመለየት የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎችንና የአጎበር አጠቃቀም ን የማሳደግ የወባ ምርመራ ላቦራቶሪ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ጥራትን በማስጠበቅ የወባ በሽታ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት እንዳይሆ የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋልም ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጡንና የኢሊኖ ክስተትን ታሳቢ ያደረገ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማጎልበት ተገቢ ነው ያሉት አቶ አብዱልዋሪስ በዞንና በወረዳ ከተሞች የRRT ቡድንኑን በማጠናከር ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች እና ወባን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎች ጫና ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የእብድ ውሻ በሽታን ከመከላከል አኳያ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየፈጸመ መሆኑ የተለጸ ሲሆን የችግሩን አሳሳቢነት ታሳቢ ያደረገ የክትትል የመከላከል ስራን በማጠናከር የንክሻ ተጎጂዎቸ ተገቢወን ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ የማህበረሰቡን ንቃተ ጤና የማሳደግ ስራን በቅንጅት ማሰለጥ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ሳምንተዊ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምልሽ አፈጻጸም ግምገማ ትርጉም ያለውና በውጤት የታጀበ ለሆን ይገባልም ተብሏል።
የወባ በሽታ ጫና ከባለፈው ዓመት በ36% ከባለፈው ሳምንት በ6% መቀነሱንና የክረምት/በጋ ዝናብን ተከትሎ ውኃ ያቆሩና ለወባ አስተላላፊ ትንኞች ምቹ የሆኑ ቦታዎችን የማፋሰስ/ማዳፈን፣ የአጎበር አጠቃቀምን ማሳደግ እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን ጥራት የማጠናከር ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።
የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነት
በቤትና በአካባቢ ውኃ ያቆሩ ቦታዎችን ማደፈን ወይም ማፋሰስ የአጎበር አጠቃቀም የወባ ስጋት ባላቸው አካባቢዎች አልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም የመረጃ ጥራትን አስጠብቆ ማስቀጠል በሳምንታዊ የውይይት መድረኩ አጽንኦት የተሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው።




