
(ሆሳዕና፣ጥር 16/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ማስጀመሪያ ፕሮግራም በሆሳዕና ከተማ ተካሒዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአሰራር ስርዓትን ማዘመን ተገቢ ነው ብለዋል።
ሀገራዊ የሪፎርም ኦሳቤን ውጤታማ ለማድረግ የአመራር ጥበብን ተጠቅሞ መፍትሄ መፈለግ ይገባል ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት ያጋገሙንን ችግሮች በመሻገር አሁን ላለንበት ደረጃ በቅተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አመራሩ የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመፈጸም ያለው ዝግጁነት ውጤታማ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
ከአመራሩ ባለፈ በፈጻሚዎች ዘንድ ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት የተሻለ እንዲሆን ያለው ተነሳሽነት እየጨመረ መምጣቱን አብራርተዋል።
ሪፎርሙን ለማሳካት አመራሩ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ተጨባጭ እቅድ ማዘጋጀት እና በቂ ተግባቦት መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በቂ አደረጃጀት እና አሰራር ፈጥሮ ወደ ተግባር ከመግባት ባለፈ ፣ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ፣ እውቀትን ሀብትን እና ገንዘብን አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ውጤት የሚያመጣና ለተሻለ ለውጥ የሚያነሳሳ የድጋፍና ክትትል ስራ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በሪፎርሙ ውጤት ማምጣት ላይ ማተኮር እንዲሁም
በችግር የተተነተኑ ጉዳዮችን መቀልበስ ይገባል ብለዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት ማስመዝገብ ተገቢ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በስራ መመሪያቸው አመላክተዋል።
የኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደ ሀገር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ ተቋም መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፈተሽ የጋራ ተግባቦት መፍጠር እንደሚገባም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ ውስጥ ዲዛይን ሲደረግ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፖሊሲው ከሀገር አቀፍ ባለፈ የአለምን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ከመንግስታዊ አገልግሎት አንጻር ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው ጉዞዎች ውጤታማ እንዳልነበር አስታውሰዋል።
እንደ ሀገር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የስራ ባህልን በማሻሻል መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
ሪፎርሙ ሁሉ አቀፍ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ትራንስፎርም በማድረግ ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
ፖሊሲው በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ለውጥ ማምጣትን ታላሚ ያደረገ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ
ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ስርዓት መዘርጋት አብይ ጉዳይ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል።
በተስፋዬ መኮንን
ለተጨማሪ መረጃ ![]()
በዌብሳይት https://www.cergcab.et/
በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB
በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL
በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225
በዩቲዩብ https://youtube.com/@centralethiopiacommunication…
በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !



