Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማህበራዊ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ከመንግሥት በተጨማሪ የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ተገለፀ።

CERPHI

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማህበራዊ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ከመንግሥት በተጨማሪ የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ተገለፀ።

ባለፉት አንድ ሳምንት አዲስ በተዋቀረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች እስከ ጤና ተቋዋማት የመስክ ምልከታ ሲያደርግ የነበረው UN -OCHA , WHO (የአለም ጤና ድርጀት ) እንዲሁም WFP (የአለም የምግብ ፕሮግራም ) የማጠቃለያ ውይይት እና የመስክ ምልከታ ግብረመልስ በቀረበበት ወቅት የተገኙት የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አንተነህ ፍቃዱ እንዳነሱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቅርብ ግዜ የተቋቋመና በአጭር ግዜ በርካታ አመርቂ ተግባራት የከወነ መሆኑን አንስተው ከክልሉ አዲስ መሆን እና በተለያዩ ግዜያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በዘላቂነት ለመቆጣጠር መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በክልሉ ገብተው ማገዝ እንዳለባቸው አሳስበው በክልሉ በኩል ማንኛውም እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል ። በውይይቱ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ክልሉን ለመደገፍም ቁርጠኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *