Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት አቀረበ፡፡

CERPHI

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት አቀረበ፡፡

በዛሬው ዕለት በክልሉ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በጋራ ለመምከር በተዘጋጀው መድረክ ላይ ሶስት የምርምር ንድፈ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ሁለቱ በወባ እና አንዱ በጤና ኬላ አተገባበር ሂደት ላያ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በውይይት ወቅት እንደተናገሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና አንድ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር የጤና ምርምር ስራዎችን ተቀናጅተው ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ (MOU) በመፈራረም ወደ ስራ መግባታቸውን በማስታወስ ፣ አሁንም በወባ እና በጤና ኬላ አተገባበር ሂደት ላይ ያተኮረ ንድፈ ሀሳብ ላይ መምከር መቻሉ በጤናው ሴክተር ለሚተገበሩ ማህበረሰብ ተኮር ተግባራት እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው የምርምር ንድፈ ሀሳቦቹ እንደ ሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ትኩረት በሚሻው የወባ በሽታና በጤና ኬላ አተገባበር ሂደት ላይ መሆኑን በማድነቅ በቀጣይ የሚመጡ የምርምር ውጤቶችም ለማህበረሰቡ ለውጥ ያላቸው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተጀመሩ የጤና ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት ለማህበረሰብ ለውጥ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲ እና ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመጡ ከፍተኛ የምርምር ባለሙያዎች እና መምህራን ንድፈ ሀሳቡን ባቀረቡበት ወቅት ጠቁመዋል ።

በመጨረሻም የክልሉ ጤና ቢሮና የኢኒስቲትዩቱ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በምርምሩ አሰራር እና አካሄድ ላይ ገንቢ የሆነ ሀሳብ አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *