Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ልማት ስራዎች አፈጻጸም እና የ100 ቀናት እቅድ ዝግጅት መድረክ ማካሄድ ጀመረ ፡፡

CERPHI

የክልሉ ጤና ቢሮ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅት እንዲሁም የአገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ስራ የሚገመግም መድረክ በወራቤ ከተማ ማካሄድ ተጀምሯል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊአቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት ጊዜያት ተጨባጭ ውጤት የተገኘባቸው ስራዎች መሰራቱን ገልጸው በመደመር መንግስት በጤናው ዘርፍ ተደማሪ ውጤት ለማምጣት ለማስመዝገብ ይሰራል ብለዋል ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድ ፕሮግራሙን በማጠናከር የማህበረሰቡን በመሰረታዊ ጤና ማረጋገጥ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል ፡፡

የመንግስት ፣የህብረተሰቡን አጋር አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ ከጤና ኬላዎች እስከ ሆስፒታሎች ግንባታ እና የማስፋፋት ስራዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል።

የመንግስት ጤና ተቋማት አገልግሎት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል ፡፡

የፈውስ ህክምና ማዕከላትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚረዱ ስራዎች መስራት እንደሚገባ ገልጸው በተለይ ከወረቀት ነጻ አገልግሎቱን ማስፋፋት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለይቶ በመፍታት ህብረተሰቡን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።

በመጨረሻም ተግባሮቻችን ከቁጥር እና ፐርሰንት ባሻገር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እርካታ መነሻ ያደረገ መሆን እንደሚገባው የቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል ፡፡

በመድረኩ ላይ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የ100 ቀናት ዕቅድ እና የአገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ዝግጅት ላይ ሰፊ ውይይት ይካሄዳል ፡፡

በመድረኩ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የማኔጅመንት አባላት የዞን እና ልዩ ወረዳ ጤና ኃላፊዎች የልማት እቅድ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል ፡፡

ዝናሽ ደለለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *