Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የኢቦላ የላቦራቶሪ ምርመራ ዝግጁነትን ለማጠናከር ስልጠና ተሰጠ

CERPHI

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች በኢቦላ የ ሞለኪውላር ላቦራቶሪ ምርመራ (Molecular Testing) ስልጠና ከUnited Kingdom Health Security Agency (UKHSA) ጋር በመተባበር ከጥቅምት 10 እስከ 14/2019 ዓ.ም ሰጠ፡፡

የስልጠናው በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል በዘላቂነት እየተከናወነ ያለው ለድንገተኛ ወረርሽኝ ላቦራቶሪዎችን አቅም በመገንባት ዝግጁ የማድረግ ስራ አንዱ አካል ሲሆን፤ ይህም ስልጠና በዋናነት በአፍሪካ አራት ሀገራት ላይ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ ፈጥኖ ለመለየትና ለመከላከል ከሚደረገው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አንጻር በአገር አቀፍ ደረጃ በየክልሉ የሚገኙ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን ዝግጁ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል መለሰ በስልጠናው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ ለማንኛውም የሕብረተሰብ ጤና አደጋና ወረርሽኞች ከመከሰታቸው አስቀድሞ የዝግጅት ስራዎችን በተለይም በሰው ኃይል፣ በላቦራቶሪ መሳሪያዎችና ግብዓቶች በኩል በቂ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።

አያይዘውም ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ከፍተኛ የምርመራ አቅም የሚጠይቁ የኢቦላ እና የማርበርግ በሽታዎችን መመርመር የሚያስችል የሞለኪውላር ላቦራቶሪ ምርመራ ስልጠና በአገር አቀፍ ደረጃ ለተደጋጋሚ ጊዜ የተሰጠ ቢሆንም፣ ባለሙያዎቹን በተሻለ ደረጃ ለማንቃትና ዝግጁነታቸውን ለማረጋገጥ ስልጠናው በተለያየ ዙር እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ የፍተሻ ስትራቴጂ (Testing Strategy)፣ የላቦራቶሪ ባዮሴፍቲ፣ ባዮሴኩሪቲ፣ የናሙና አሰባሰብ እና አላላክ መመሪያዎች (ጋይድላይኖች) እንዲሁም ተያያዥ ፕሮቶኮሎች በኢንስቲትዩቱ በኩል ተዘጋጅተው ተሰራጭተዋል፡፡

በተጨማሪም በክልል ላቦራቶሪዎች በኩል ሊኖሩ የሚችሉ የዝግጅት ክፍተቶችን የመለየት፣ የማሟላትና የማዘጋጀት ሥራ ቀድሞ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንን ጥረት የበለጠ ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ መድረክ ላይ ሰልጣኞች እንዳሉት፤ ሥልጠናው በአብዛኛው በሞለኪውላር ላቦራቶሪ የተግባር (Practical) ክፍለ-ጊዜ ላይ በማተኮሩ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ እንዳስገኘላቸው ገልጸዋል፡፡

A Training was Conducted on Ebola Lab Testing Preparedness

———————————————

The Ethiopian Public Health Institute (EPHI), in collaboration with the UK Health Security Agency (UKHSA), successfully conducted a five-day capacity-building training on Ebola molecular testing for laboratory professionals from across regions from Octobe20 to 24, 2026 at EPHI.

The training is part of EPHI’s on going activities to strengthening regional laboratory diagnostic capacity and enhancing preparedness for public health emergencies.

Through intensive hands-on sessions, participants improved their skills in Ebola molecular testing, laboratory biosafety and biosecurity, sample collection and transport, and outbreak response protocols. Speaking during the training, Daniel Melesse, Director of EPHI’s Capacity Building Directorate, emphasized the Institute’s continued efforts to ensure readiness for emerging public health threats through investments in skilled personnel, laboratory infrastructure, equipment, and supplies.

Participants highlighted the practical nature of the training, noting that it provided valuable knowledge and experience to support rapid detection and response to Ebola and other high-risk infectious diseases.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *