
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ100 ቀን ዕቅድ ገምግሟል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ100 ቀን ዕቅድ በተመለከተ ከዘርፉ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብድልዋሪስ ጀማል በዚሁ መድረክ ላይ እንደገለፁት ባለፉት ሦስት ወራት የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የበለጠ ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን በየደረጃው ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በኢንስቲትዩቱ የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይበልጥ ማስፋት ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ዉጤታማነቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
በኢኔስቲትዩቱ የሚነሱ ማነቆዎችን ፈጥኖ መለየት ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለሚነሱ ችግሮቹ ተገቢዉን መፍትሄ በማበጀት በጊዜ መፍታት ይገባል
መድረኩ በቀሪው በጀት ዓመት በቅንጅትና በትብብር የታቀዱ ተግባራትን በተሻለ መንገድ ለማከናወን እንደሚያግዝም አቶ አብድልዋሪስ አስታውቀዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በበኩላቸው በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ዘላቂና የማይበገር የላብራቶሪ ሥርዓት በመገንባት ጥራት ያለው አገልግሎትን ለማረጋገጥ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በባለፉት ሦስቱ ወራት ዉስጥ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠንካራ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።
የጥናትና ምርምር ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆናቸውን የገልፁት አቶ ለገሰ የመረጃ ሥርዓቱም የተሻለ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በግምገማው መድረክ በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ የተወያየ ሲሆን፣ የተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በተግባራዊ ዕቅዶች ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጧል።
በቀሪው የበጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራትን በቅንጅት፣ በትብብርና በተጠያቂነት በመፈጸም የሕብረተሰብ ጤና ሥርዓቱን ማጠናከር ይጠበቃል።
በሸምሲያ አደም

