Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ሳምንታዊ ግምገማ ተካሄደ ፡፡

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ሳምንታዊ ግምገማ ተካሄደ ፡፡

በክልሉ ድንገተኛ የጤና እና የተፈጥሮ አደጋዎችን የቅኝትና ምላሽ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት ተደርጓል።

በምግብ እጥረትና በወባ በሽታዎ እንዲሁም በመረጃ አያያዝ ተግባራት ላይ እና በሌሎች የጤና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል ።

የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የወባ በሽታ ጫና ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ የክትትል እና የአካባቢ ቁጥጥር ሥራዎችን ማጎልበት እንደሚገባ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ ገልጸዋል ፡፡

የምግብ እጥረት በሽታ ጫና ያለባቸውን ወረዳዎች በመለየት ህፃናት በምግብ እጥረት እንዳይጎዱ ጥራት ያለው የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን ማጠናከር ይገባልም ሲሉም አስታውቀዋል።

ወቅቱን የሚመጥንና ዘመኑን የዋጀ የመረጃ አያያዝ አደረጃጀት እና የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን የተሳለጠ እንዲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት አቶ ትክክለኛ መረጃን በወቅቱ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀባበል የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኬሚካል መመረዝን ጨምሮ ሌሎች የጤና ጉዳዮች የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ሆነው እንዳይቀጥሉ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ ናቸው።

በቀረበው ሳምንታዊ ሪፖርት መነሻ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት ፈጣን ምላሽ ለሚሹ ምላሽ የመስጠትና መጠናከር በሚገባቸው ጉዳዮች መግባባት ላይ ተደርሷል።

ዝናሽ ደለለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *