
ኢንስቲትዩቱ የአደጋ ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ባካሄደው ሳምንታዊ ስብሰባውን የህብረተሰብ ጤና ሁኔታ፣ የበሽታ ክትትል፣ መረጃዎችን እና የተወሰዱ የምላሽ እርምጃዎችን ገምግሟል።
የEOC ቡድኑ በሳምንታዊ ስብሰባዉ የክልሉን ነባራዊ የጤና ሁኔታ ፣ ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት ሊሆኑ በሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ዙሪያ፣ የበሽታ ስርጭት፣ የተለያዩ ወረርሽኞች፣ሪፖርቶች እና የምላሽ አፈጻጸም ሂደትን ገምግሟል።
አቶ በዓሉ በቴቦ የኢንስቲትዩቱ የቅኝት እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኬዝ ቲም አስተባባሪ መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ የሚከሰቱ የውሻ ንክሻ ክስተቶችን በመከታተል የቅድመ መከላከልና የፈጣን ምላሽ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።
የወባ በሽታን በዘላቂነት ለመግታት በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች የአጎበር ስርጭት መደረጉን የጠቆሙት አቶ በዓሉ ከአጎበር አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለዉን ክፍተት ለመሙላት አስተማሪ እና ተከታታይነት ያለዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ይገባል ።
በጤና ተቋማት የሚገኙ የላብራቶሪ ተግባራትን ማጠናከር ወሳኝ ነዉ ያሉት አስተባባሪዉ የናሙና ቅበላ፣ ምርመራ፣ የውጤት ማረጋገጫ እና የሪፖርት አደራረግ ሥራዎችን በጥራት ማከናወን ይገባል ብለዋል።
ወቅቱን የጠበቀ የጤና መረጃዎችን በጥራት በማደራጀት እና በመተንተን ለቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ለፈጣን ምላሽ የሚያግዙ ውሳኔዎችን ጥቅም ላይ የማዋል ባህልን ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል
በመድረኩ በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን
ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ መጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ዉይይቱ ተጠናቋል።
በሸምሲያ አደም


