
ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ የተሰኘው ድርጅት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት ወረርሽኝን የመከላከል አቅማቸውን ለማሳደግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ሲያካሂድ የነበረውን የሙከራ ትግበራ አጠናቆ አስረክቧ።
የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድን (Primary Care) ማጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ካሉ አምስት ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው መሆኑን የጤና ሚኒስትር ድዔታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገልፀዋል።
የማይበገር የጤና ሥርዓት መገንባት የሚቻለው የጤና ተቋማት ወረርሽኝን የመከላከል፣ የመዘጋጀትና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅማቸው ጠንካራ ሲሆን መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ደረጄ፤ በተለይም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አሃድ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ቀድሞ በመለየትና ሳይዛመቱ በተከሰቱበት አካባቢ ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስገንዝበዋል
ዶ/ር ደረጄ ክለውም አጋር ድርጅቶችም የመንግሥትን ስትራቴጂ ተከትለው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በአሁኑ ወቅት በ197 የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የተጀመሩ የሙከራ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በማስፋፋትና ወደ ሙሉ ትግበራ በማሸጋገር፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ሥራን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና ጠንካራና አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ኢንስቲትዩት እና በጉዳዩ ላይ ከሚሰራው ከሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይፍ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ፕሮግራም የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች በጉዳዩ ለይ የሚሰሩ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
