
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ Biosafety and Biosecurity program Implementation ተገምግሞ፣ የኮከብ ደረጃ-አራት (Star Level- 4) የዕውቅና ሰርተፍኬት ማግኘቱን በማስመልከት፣ የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ላቦራቶሪ በመገኘት የላቀ ውጤቱ እንዲመዘገብ ትልቅ አስተዋጽኦ ላባረከቱት አጠቃላይ ሠራተኞችን አመስግነዋል።
የክልሉ ህ/ጤ/ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እና ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ፣ የክልሉ ላቦራቶሪ በBiosafety and Biosecurity ፕሮግራም ትግበራ STAR-LEVEL 4 (![]()
![]()
![]()
) እውቅና ሰርተፊኬት በማግኘቱና ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት፣ በላቦራቶሪው በመገኘት ደስታቸውን ገልጸው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይም ያገኘነውን እውቅና በሚያስጠብቅበት ሁኔታ እንዲሁም በጤና ተቋማት ደረጃ የሚተገበረውን አጠቃላይ የላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር አመራር ትግበራ ( Laboratory Quality Management Implementation) ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ለዚህ ሥራ የሚያስፈልገው ድጋፍ በሚመለከት የአመራሮቹ ሙሉ ድጋፍ እንደማይለይ ቃል ገብተዋል።
የክልሉ ላቦራቶሪ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚተገበሩ አዳዲስ ኢንሼቲቮች በመተግበር ተወዳዳሪ ላቦራቶሪ ለመገንባት እንደሚሰራ በመግለፅ፣ ላቦራቶሪው በሁሉም ዘርፍ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ኢንስቲትዩቱ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።
መረጃ ምንጭ – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህ/ጤ/ኢንስቲትዩት

