Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሄደ ፡፡

CERPHI

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሄደ ፡፡

8/7/18 ዓ/ም ወራቤ

ኢንስትቲዩቱ ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ዙሪያ ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል።

የጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ከለላዉ አቻምየለህ የሳምንቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከል በየደረጃው በተሰሩ ስራዎች በሳምንቱ 13 በመቶ የወባ በሽታ መቀነሱን ጠቁመዋል

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የዚህን ሳምንት ቅኝት ሲያብራሩ ማህበረሰቡን ከተለያዩ የጤና ስጋቶች ቀድሞ ለመከላከል እና ማንኛዉም ወረርሽኝ ሊከሰት የሚችልበትን ወቅቶችን ቀድሞ በመተንበይ በሽታዉ ጉዳት እንዳያደርስ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የወባ በሽታ በጤና ተቋማት የምርመራ እና የህክምና አገልግሎትን ማጠናከር እንደሚገባ የገለፁት ደይሬክተሩ ወቅቱን የጠበቀ የመረጃ ልዉዉጥ ስርዓታችንን በማጎልበት ትክክለኛ መረጃን ማደራጀት እንደሚገባም ዳይሬክተሩ አንስተዋል ።

የወባ በሽታ ያልቀነሰባቸዉ አካባቢዎችን በመለየት የቅኝት ስራችን ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት አቶ ወልደሰንበት ማህበረሰቡ የራሱን ጤና በተገቢዉ እንዲጠብቅ ግንዝያቤያቸዉን ማሳደግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናት የልየታ እና የህክምና አሰጣጡን ወደ ታች በመዉረድ ተገቢዉን ክትትል ማድረግ ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ የሚዝል ክትባት በአግባቡ አየተሰጠ ስለመሆኑ የቅኝት ስራዎች መጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመድረኩም በክልሉ የወባ ወረርሽኝ እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *