Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በክልሉ በሚገኙ መዋቅሮች በተደረገዉ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸዉ ተመላከተ ፡፡

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት በየመዋቅሮች የተከናወኑ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተቀናጀ የድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።፣

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለፁት በየደረጃዉ በሚገኙ የጤና መዋቅሮች በተደረገዉ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸዉን ጠቁመዋል ።

አቶ ማሙሽ የፌም ስርዓትን ለመገንባት አደረጃጀትን፣ አሰራርን እና የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በማጠናከር ተግባሮቻችንን ይበልጥ ዉጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል

አደረጃጀትን ለመተግበር የመጀመሪያው ብቁ የሰው ሀይል መፍጠር ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ማሙሽ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት የዳታ ቤዝ አሰራርን በማጠናከር ከተደራጀው የሰው ሀይል ፕሮፋይል ቋት ውስጥ ብቁ ባለሙያዎችን በመውሰድ ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አደረጃጀትን ከማጠናከር አንፃር ባለሙያውን ማሰልጠን እና በግብዓት የተሟላ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ስራውን በቴክኖሎጂ ለማቀናጀት ሁሉም አካባቢ ላይ በዕቅድ ቅደም ተከተል የዲጂታላይዜሽን ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የፌም አቅምን ለማሳደግ ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ረገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ያነሱት አቶ ማሙሽ በዋናነት ያጋጠሙ ችግሮችን መለየት እና መፍትሄ በማመላከት እንዴት እንስራው የሚለው ጉዳይ በተገቢው በመገምገም መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ ማሙሽ በማጠቃለያው ላይ በሁሉም ዘርፍ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰዉ በድጋፍና ክትትል እንዲሁም በጥናት ክፍተቶችን በመለየት እና ስልጠና በመስጠት ዘርፉን ይበልጥ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *