Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ለጤናና ጤና ነክ አደጋዎችና ወረርሽኞች የማይበገር ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

CERPHI

የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዓመት የባለፉት ስድስት ወራት የዕቅድ ክንዉን አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በዱራሜ ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ በበጀት አመቱ በባለፉት 6 ወራት በዘርፉ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት (Preparedness)፣ የቅኝትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ (Surveillance & Early Warning)፣የድንገተኛ አደጋዎች የምላሽ (Response) ተግባራትና የPHEM DHIS2 አተገባበር ዙሪያ የመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀምን በሚመለከት እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተግባራት የዞኑ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በተጨማሪም የየመዋቅሮቹን የአፈጻጻም ሪፖርት በዘርፉ አስተባባሪዎች ለተሳታፊዎች ቀርቦ በበጀት አመቱ አፈጻጸም በየደረጃው የተለዩ ችግሮችን በመፍታትና መልካም ተሞክሮዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚረዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት ተደርጓል።

የግምገማ መድረኩን ያስጀመሩት የዞኑ ጤና መምሪያ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ አሥራት ቆልቻ ባስተላለፉት መልዕክት የጤና ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የጤናና ጤና ነክ አደጋዎች የማህበረሰቡ ችግር ወደ ማይሆኑበት ደረጃ ለማድረስ በበጀት አመቱ የበሽታዎች ክስተት ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ተጠናክረው እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዉ በበጀት አመቱ ባለፉት 6 ወራት በወረርሽኝ መልክ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን አስቀድሞ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

አቶ አሥራት አክለዉም በበጀት አመቱ በባለፉት 6 ወራት የተሻለ ዉጤት ያስመዘገብናቸዉ ተግባራትን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎችን በማጠናከር፣በየደረጃዉ ካሉ የባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር እንዲሁም የጤና ሴክተሩን አቅም በማጎልበት ለወራርሽኝ የማይበገር የጤና ሥርዓትን መፍጠር የቀጣይ የሴክተሩ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በግምገማ መድረኩም በቀሪ ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸዉ ሊከናወኑ በሚገባቸው ቁልፍ በሆኑ ተግባራት ከመድረኩ ተሳታፊዎች የጋራ መግባባት የተፈጠረ ሲሆን በመጨረሻም ከየመዋቅሩ የዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር የበጀት አመቱ ቀሪ ወራት ዕቅድ ዙሪያ የግብ ስምምነት ፊርማ ሥነስርዓት በማካሄድ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ ከዞኑ መዋቅሮችና ከጤና ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣የዞኑ ጤና መምሪያ ማናጅመንት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *