Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ከጥቃቅን ንጥረ ምግቦች (multiple micronutrient supplementation) የሚዘጋጀ እንክብል በእርግዝና ወቅት ለነፍሰጡር እናቶች መስጠት ጠቃሚ ነው!

CERPHI

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች፣ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በጥናትና በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክልሎች ለነፍሰጡር እናቶች ሲሰጥ የነበረው የMMS (multiple micronutrient supplementation) ወደ ሌሎች ክልሎችና ወረዳዎች የማስፋፊያና ማስተግበሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ባስተላለፉት መልዕክት ለነፍሰጡር እናቶች በወሊድ ክትትል ወቅት የሚሰጥ ከጥቃቅን ንጥረ ምግቦች የተዘጋጀ እንክብል በጥናትና በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክልሎችና ወረዳዎች ሲተገበር የነበረው የሙከራ ትግበራ ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በሌሎች ክልሎችና ወረዳዎች የማስፋፊያ ትግበራ ይከናወናል ብለዋል::

በመላ ኢትዮጵያ የእናቶች እና ህጻናትን ጤና አገልግሎትን የሚያሻሽል እና ነፍሰ ጡር የሆኑ እናቶች በወሊድ ክትትል ወቅት እንክብሉን እንዲጠቀሙ አስፈላጊው የግንዛቤ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን አንስተው በጥናቱ እና በትግበራው ውጤታማ ስራ ላይ አስተዋጽኦና ተሳትፎ ላደረጉ ክልሎች፣ ተቋማትና አጋር ድርጅቶች እና ባለሙያዎች ሚኒስትር ዴኤታው ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ወ/ሮ ህይወት ዳርሰኔ በጤና ሚኒስቴር የስርዓት ምግብ ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው በጥናትና በሙከራ ትግበራ ደረጃ ለነፍሰጡር እናቶች ከጥቃቅን ንጥረ ምግቦች የተዘጋጀ እንክብል በ70 ወረዳዎች ሲሰጥ እንደቆየ አክለው እንክብሉ እናቶች ነፍሰጡር ከሆኑ ጀምሮ የተሻለ የእርግዝና ሂደት እንዲኖራቸው የሚያደርግና ጤናማ ልጆች መውለድ እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ ጠቁመው ወደ ሌሎች ክልሎችና ወረዳዎች ተደራሽነቱን ለማስፋፋትና ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለማስገባት በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል::

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *