
የአፍሪካ ቀንድ የወባ ሞለኪውላር ክትትል ዓመታዊ የግምገማ ስብሰባ ተካሂዷል፣ በስብሰባው ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ ሳይንቲስቶችን እና አጋሮችን በማሰባሰብ የምርምር ግኝቶችን ገምግሟል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንዳሉት የሞለኪውላር ክትትል ተነሳሽነት ወባን በተሻለ ሁኔታ ለመዋጋት ጥቅም ላይ የሚውል ተጨባጭ ማስረጃዎችን አስገኝቷል። በአመቱ በአንዳንድ አገሮች የወባ በሽታ የጨመረ ቢሆንም፣ በተሰራዉ የተቀናጀ ስራ ዉጤትም መገኘቱን ተናግረዋል።
ዶ/ር መቅደስ የወባ ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት መጀመሩን አፅንዖት ሰጥተው የወባ በሽታን የመከላከል ጥረቶችን በተመለከተ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በጥናቱ የተገኘው መረጃ ለፖሊሲ፣ መከላከል እና የሕክምና ግብአቶችን ለመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የአርማሁር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዪት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው አመታዊው የግምገማ መድረኩ ከቀጣይ የሞለኪውላር ክትትል ጥናት የተገኙ ቁልፍ ግኝቶችን በመወያየት ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል። ስብሰባው ቴክኒካዊ መመሪያ ለመስጠት እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥን ለመደገፍ ሳይንሳዊ አማካሪ ኮሚቴ መቋቋሙን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ለወባ እና ለሌሎች የህብረተሰብ ጤና ስጋቶች ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ የጤና ስርዓቶችን ስለመገንባት ውይይቶች መካሄዱን ተናግረዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB





