Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ28ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 34 የጤና ተማሪዎችን አስመረቀ።

(ሆሳዕና፣ ጥር 23/2018 ዐ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በደረጃ 4 እና በዲግሪ ፕሮግራም በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ለ28ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 34 የጤና ተማሪዎች አስመርቋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳና የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት የክልሉ መንግሥት በጤናው ሴክተር ለማሳካት ካስቀመጣቸው የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅዶች አመርቂ ውጤት ተገኝቷል።

በቤተሰብ ደረጃ የበለጸገ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጉዞ ላይ የዕለቱ ተመራቂዎች ጉልህ ሚና ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ሳሙኤል አስገንዝበዋል።

የጤናው ባለሙያ ኃላፊነት በገንዘብ የማይተመን በመሆኑ የዕለቱ ተመራቂዎች ሙያዊ ሥነ ምግባር በመላበስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የዕለቱ የክብር እንግዳ አደራ ብለዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤናው ዘርፍ ሁለንተናዊ ብቃት የተላበሱ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች በትምህርትና ሥልጠና ያሳዩትን ትጋትና ጽናት በሥራ ዓለምም በመድገም የሰው ልጆችን ሁሉ በሙያዊ ስነ ምግባርና በሰብዓዊ ርህራሄ እንዲያገለግሉ አቶ ማሙሽ አሳስበዋል።

የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ኤልያስ ቲራጎ በኮሌጁ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ታግዞ ለመስጠት የተጀመረው ሥራ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

በጤናማ ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጤና ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የዕለቱ ተመራቂዎች ሚናቸውን እንዲወጡ አቶ ኤልያስ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎችም በመርሃ-ግብሩ የሙያ ቃለ-መሃላ የፈጸሙ ሲሆን ከተመረቁ 1ሺህ 34 የጤና ተማሪዎች ውስጥ ከ63 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ለመወቅ ተችሏል።

በተያያዘ ዜና ኮሌጁ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር ያለመው የተማሪዎች መረጃ አስተዳደር ቋት ማዕከል የተመረቀ ሲሆን ማዕከሉም ኮሌጁ የሚሰጠውን የተማሪዎች አገልግሎት ከእጅ ንክኪ ነጻ በማድረግ ጥራትና ቅልጥፍናን የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል።

በአሳምነው ተከተል

የቢሮውን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት

📌 በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678

📌 በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225

📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/@centralethiopiacommunication…

📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *