
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ/ም ዓመታዊና የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክ/ሀላፊና የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለፁት የህብረተሰቡን የጤና ስርዓት መገንባት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱን በሰው ሀይል እና ሎጀስቲክ ከማሟላት አንፃር እንዲሁም የተለያዩ ወረርሽኞችን ከመቀነስ ረገድ ዉጤት መመዝገቡን አስረድተዋል ።
ለዞኖች የታብሌትና የኮምፕዉተር ግብዓቶች መሰራጨቱን ያነሱት አቶ ማሙሽ የተላለፈዉን የስራ ቁሳቁስ ለታለመለት ዓላማ ብቻ ማዋል እንደሚገባ አመላክተዋል ።
ክልሉ ለወባ በሽታ ስጋት መሆን የለበትም ያሉት አቶ ማሙሽ እናቶች፣ ህፃናት እና ቤተሰብ በወረርሽኝ መሞት ስለሌለባቸው ወረርሽኝን በጋራ ተቀናጅተን ለማጥፋት ርብርብ ማድረግ ይገባል ።
በቀጣይ የጤና ስርዓቱን በማጠናከር በተጠያቂነትና በባለቤትነት ተግባሮቻችን በመፈፀም የተመዘገበውን ዉጤት ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ ማሙሽ አሳስበዋል
የክልሉ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም በህብረተሰቡ ላይ የሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባሩ ዉጤታማ መሆኑን ገልፀዋል
በክልሉ ጠተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በቅንጅትና በትብብር ሰፋፊ ስራዎች በመከናወናቸው ተጨባጭ ዉጤት መመዝገቡን ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል ።
በ2016 ዓ/ም ከ2 ሺህ በላይ የኩፍኝ በሽታ መከሰቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6መቶ ኬዝ ብቻ መከሰት እና የሞት ምጣኔ ያልተመዘገበበት ዓመት እንደነበር አስረድተዋል ።
በክልሉ የኮሌራ በሽታ፣ የክትባት ተደራሽነት፣ እንዲሁም የወባ ኬዝ በተሰራዉ ጠንካራ ስራ አመርቂ ዉጤት መመዝገቡንም አቶ ወልደሰንበት አክለዋል ።
የተከሰቱ በሽታዎችን በመለየት እና ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት እንዲሁም የሚፈጠሩ ችግሮችን በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም እና አስተያየት የመስጠት ልምዱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በክልሉ ለሁሉም ዞንና ልዩ ወረዳ የፌም ተግባርን በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ መደረጉን ያነሱት ዳይረክተሩ ለቴክኖዎሎጂዉ ስራዉ አጋዥ እንዲሆን ግብአት በሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ መደረጉን ምአቶ ወልዴ አክለዋል ።
በመድረኩ በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ የስራ አቅጣጫን የሚያመላክት ሰነድ በአቶ ወልደሰንበት ሸዋለም ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል ።
የጤና ቢሮ የማነጅመንት አባላት፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር የፌም ባለሙያዎች እና የጀነራል ሆስፒታሎች የፌም ባለሙያዎች በመድረኩ ተሳታፊ ነበሩ።



