
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ለወረዳዎች ታብሌት ድጋፍ አደረገ:- ጥቅምት 10/2018:- ቁሊቶ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ያበረከታቸው ታብሌቶችን በዛሬው ዕለት ለወረዳዎች አስረክቧል ።
ዶ/ር ሸምሱ ረሽድ ባደረጉ የመክፈቻ ንግግር ለድንገተኛ ወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት በመገንባት በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞች በማህበረሰቡ ላይ የከፋ የጤና ጉዳት አንዳያደርሱ በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ የጤና አገ/ት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመረጃ ስርዓቱን ወቅቱን በሚመጥንና ዘመኑን በዋጀ ሂደት ለመምራት እና በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በአፋጣኝ መቆጣጠር የሚያስችል የመረጃ ስርዓቱን ለማሳለጥ በዛሬው ዕለት በስጦታ የሚበረከቱ ታብሌቶችኛ ላፕቶፖች አጋዥ መሆናቸውን በማመላከት ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የመምሪያዉ ሀላፊ ጠይቀዋል።
ዶ/ር ሸምሱ ረሺደ ባስተላለፉት መልዕክት የመረጃ ጥራት ለይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ
